top of page

በመገኛኛ ብዙሃን ሴቶችና ህፃናት የሚወከሉበት መንገድ  መብቶቻቸውን  ጥያቄ ውስጥ የሚከት መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ተናገረ፡፡

  • Feb 24
  • 2 min read

የካቲት 17/2018

 

በመገኛኛ ብዙሃን ሴቶችና ህፃናት የሚወከሉበት መንገድ  መብቶቻቸውን  ጥያቄ ውስጥ የሚከት መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ተናገረ፡፡

 

ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም ባደረኩት ክትትል ትኩረት የሚያስፈልጋቸውና አብዛኛውን የማህበረሰብ ክፍል የሚይዙት የሴቶችና ህፃናት መብት አጠባበቅ ላይ መሻሻሎች ቢኖሩም በተለይ በመገናኛ ብዙሃን ሲቀርቡ በሚገባቸውን ልክ ይወከላሉ ወይ? የሚለው ጉዳይ ላይ ብዙ ክፍተቶችን ተመልክተናል ብሎናል፡፡

 

የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት በእለት ተእለት ስራቸው መብቶቻቸውን ላለመጣስ የሴቶችና ህፃናት መብቶችን ለመጠበቅ የወጡ አዋጆችንና ድንጋጌዎችን እየፈተሹ መስራት ላይ ችግሮች አሉ ያሉን በኮሚሽኑ የሴቶችና ህፃናት የስራ ክፍል ዳይሬክተር የሆኑን ወ/ሮ ሰላማዊት ግርማይ ናቸው፡፡

 

በተለያዩ ዘገባዎች ስለ ሴቷ በአብዛኛው ሽፋን የሚሰጠው በማህበረሰቡ ዘንድ እንድትገለጽ በሚፈለግበት መንገድ እንጂ እንደ አንድ ሰው መብቷን በሚያስጠብቅ መልኩ አይደለም ይላሉ፡፡

 

በሌላ በኩል ህፃናት በመገናኛ ብዙሃን የዜናና የፕሮግራም ሽፋን እነርሱን የተመለከቱ ጉዳዮች፣ስለ መብታቸው፣ ስለ አስተዳደር አኗኗራቸውና ስለ ሌላውም ትኩረት ሲሰጥ አይስተዋልም የሚሉት ወ/ሮ ሰላማዊት ሽፋን ቢሰጥ እንኳን ስለ ህጻናት ጉዳይ ወላጆችና ሌላው ባለሙያ ሃሳብ እንዲሰጥ እንጂ ህፃናቱ እንዲያወሩ አይፈቀድላቸውም፤ ይህ የመጣው ደግሞ ምንም አያውቁም በሚል ሃሳባቸውን አሳንሶ ከማየት ነው፤ ይህ ሌላው የሚዲያው ችግር ነው ብለውናል፡፡

 

ተቆጣጣሪ አካል የሆነው የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን በበኩሉ በመገናኛ ብዙሃን የሚቀርቡ ይዘቶችን ጠቅሶ በዚህ መንገድ መብቴ ተጥሷል ብሎ ቅሬታውን ይዞ የመጣ የለም ብሏል፡፡

 

በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የሴቶችና ህፃናት ዳይሬክተሯ ወ/ሮ ሰላማዊት ግርማይ ቅሬታዎች አልመጡም ማለት የመብት ጥሰት የለም ማለት አይደለም፤ ድምጽ የሚሆን ሰው አለመኖሩን ነው የሚያሳየው፤ የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን እንደ ተቆጣጣሪ አካልነቱ ወረድ ብሎ ጉዳዩን ቢፈትሸው መልካም ነው ሲሉም ያስረዳሉ፡፡

 

ይህ ህፃናትና ሴቶች ሃሳባቸውን በተገቢውና ይገባናል በሚሉት መንገድ የሁሉም በሆነው ሚዲያ እንዳያንፀባርቁ የሚያደርገው ተለምዷዊ አሰራር፤የሚወከሉበት የተዛባ መንገድ፤ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን የሚገድብ፤ ሰብዓዊ ክብር የማግኘት መብትን የሚጋፋ እንደሆነም የሚናገሩት ሃላፊዋ፤ ከመገናኛ ብዙሃንና ከተቆጣጣሪ አካላት ጋር በምናደርጋቸው ንግግሮች የሚታዩ ችግሮች እንደሚስተካከሉ ከስምምነት ላይ እንደደረሱም ጠቁመዋል፡፡

 

ሙሉ ዘገባውን  ለማድመጥ….

 

ምንታምር ፀጋው

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

YouTube : https://shorturl.at/18TS1                   

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page