top of page

በመንገድና ትራንስፖርት ዘርፍ ለሚታዩ ችግሮች መፍትሄ ይሰጣል የተባለ ፖሊሲ እየተረቀቀ እንደሚገኝ ተነገረ

  • sheger1021fm
  • Dec 17, 2025
  • 1 min read

ታህሳስ 8/2018

 

ህገ ወጥ ኬላዎችን እና የኮቴ ክፍያን ጨምሮ በመንገድና ትራንስፖርት ዘርፍ ለሚታዩ ችግሮች መፍትሄ ይሰጣል የተባለ ፖሊሲ እየተረቀቀ እንደሚገኝ ተነገረ

 

ረቂቅ ፖሊሲው እየተሰናዳ ያለው በትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር እንዲሁም በከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር እንደሆነ ሰምተናል።

 

ሁለቱ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ለእዚሁ የመንገድና ትራንስፖርት ረቂቅ ፖሊሲ የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ ትናንት አካሂደዋል።

 

የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስትሩ አለሙ ስሜ(ዶ/ር) ፖሊሲው ቀጠናዊ ትስስር እውን እንዲሆን እንዲያግዝ፣ ዘመኑ ያፈራቸውን ቴክኖሎጂዎች መጠቀምን እንዲያበረታታ እና በመንገድና በትራንስፖርት ዘርፍ ያለውን ችግር እንዲፈታ ሆኖ የተዘጋጀ ነው ብለዋል።

 

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትሯ ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ በበኩላቸው መንገዶች ከተገነቡ በኋላ የሚታዩ የቁጥጥር እና ክትትል ክፍተቶቸን ለመፍታት እየተዘጋጀ ያለው ፖሊሲ አንደሚያግዝ ተናግረዋል።

 

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….

 

ፍቅሩ አምባቸው

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

  

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page