በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ታድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና የልብስ ቁራጮች እንዲሁም የወርቅ አምባር ቅርሶች ከ158 ዓመታት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል፡፡
- May 14
- 1 min read
ግንቦት 6/2018
በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ታድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና የልብስ ቁራጮች እንዲሁም የወርቅ አምባር ቅርሶች ከ158 ዓመታት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል፡፡
ቅርሶቹ የተመለሱት ከእንግልዝ ሀገር ሲሆን ቅርሶቹን ያመጡት ሮቢን ጃክሴን (ዶ/ር) የእንግልዝ የንግስቲቱ ቤተሰብ ሙዚየም ኃላፊና አሉላ ፓንክረስት (ዶ/ር ) የኢትዮጵያ ቅርስ አስመላሽ ኮሚቴ አባልና ተመራማሪ ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አበባው አያሌው እና የኢትዮጵያ አርበኞች ማህበር አባላት ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት በመገኘት ለቅርሶቹ ደማቅ አቀባበል አድርገዋል፡፡
የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አበባው አያሌው ታሪካዊ የሆኑ ቅርሶች በተለያዩ ምክንያቶች ከሀገር ውጭ የወጡትን ወደ ኢትዮጵያ የመመለስ ስራ በትልቅ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን አብራርተው በተለይ በዘንድሮ ዓመት አመርቂ የሆነ ስራ የተሰራበት ዓመት ነው፣ ትልቅ የዲፕሎማሲ ስኬትም የተገኘበት ዓመት ነው ብለዋል፡፡
ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ የገቡት ቅርሶች በነገው ዕለት ግንቦት 7/2018ዓ.ም በባለስልጣን መ/ቤቱ የቅርሶቹ ርክክብ እንደሚደረግ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ተናግሯል፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv





Comments