ሰኔ 20፣2015
በሌተናል ጄኔራል ሐምዳን ዳጋሎ የሚመራው ፈጥኖ ደራሽ ሀይል በካርቱም የሚገኘውን የሱዳን ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያን ተቆጣጠርኩት አለ፡፡
RSF የተሰኘው ፈጥኖ ደራሽ ሀይል በካርቱም የሚገኘውን የፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ መያዙን አስመልክቶ መግለጫ እንዳወጣ ሜኸር ድረ ገፅ ፅፏል፡፡
ፈጥኖ ደራሹ ታጣቂዎቹ ጠቅላይ መምሪያውን መቆጣጠራቸውን የሚያስተማምኑ ፎቶ ግራፎችን እዩልኝ ማለቱም ታውቋል፡፡
RSF የፖሊስ ጠቅላይ መምሪያውን የተቆጣጠረው ካለፈው ቅዳሜ አንስቶ ሲካሄድ በነበረው ከባድ ውጊያ ነው ተብሏል፡፡
የፈጥኖ ደራሹ ሀይል የተቆጣጠረው የፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የበርካታ ጦር መሳሪያዎች እና ጥይቶች መገኛ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡
በሱዳን መንግስት ጦር እና በፈጥኖ ደራሹ ሀይል መካከል ውጊያው ከ11 ሳምንታት በላይ ሆኖታል፡፡
የኔነህ ከበደ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
https://bit.ly/33KMCqz
Comments