top of page

ህዳር 6፣2016 - ''በላሊበላ ውቅር አቢያተ ክርስቲያናት ላይ ጉዳት ደርሷል በሚል የሚሰራጨው መረጃ ትክክል አይደለም'' የቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን

በአማራ ክልል ባለው ወቅታዊ ሁኔታ የተነሳ በላሊበላ ውቅር አቢያተ ክርስቲያናት ላይ ጉዳት ደርሷል በሚል የሚሰራጨው መረጃ ትክክል አይደለም ሲል የኢትዮጵያ የቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ተናገረ፡፡


ባለስልጣን መ/ቤቱ የራሴን ቡድን ልኬ በአቢያተ ክርስቲያናቱ ላይ በጦርነት ምንም ጉዳት እንዳልደረሰ አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡


ፍቅሩ አምባቸው

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

bottom of page