top of page

በህግ ላይ ያለው ክፍተት በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች መልካቸው እየቀያየሩ እንዲበረክቱ አድርጓል ተባለ

በወንጀለኛ መቅጫ ህግ ላይ ያለው ክፍተት በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ፆታዊና አካላዊ ጥቃቶች መልካቸው እየቀያየሩ እንዲበረክቱ አድርጓል ተባለ፡፡


ሴቶች የሚደርሱባቸውን ፆታዊ እና አካላዊ ጥቃቶች ተከትሎ በወንጀለኞች ላይ የሚሰጠው ብይን ተመጣጣኝ ባለመሆኑ ፍትህን እያዛባ እንደሆነ ተነገሯል፡፡


ጥቃት አድራሹ ጥቃቱን ካደረሰ በኋላ ወደ ፍርድ ሲቀርብ ለፈፀመው ወንጀል የሚጣልበት ቅጣት ተመጣጣኝ አለመሆኑን በሴቶች መብቶች ላይ የሚሰሩ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እየሞገቱ ነው፡፡


በሴቶች ጥቃት ዙሪያ የወጣው ህግም እራሱ ክፍተት እንዳለበት የተነገረ ሲሆን ቀደም ብለው ከወጡ የወንጀለኛ መቅጫ ህጎች ተሻሽሎ የወጣ ቢሆንም ግን ሴቶች ላይ ከሚፈፀሙ ወንጀሎች አንፃር አስተማሪ ፍርድ እንዲሰጥ የሚያደርግ አይደለም የሚል ትችት ቀርቦበታል፡፡


የወንጀኛ መቅጫ ህጉ አስተማሪ አለመሆኑ ሴቶች ላይ የሚደርሰው ፆታዊም ሆነ አካላዊ ጥቃት አይነቱን እየቀየረ እና እየከፋ መጥቷል ሲሉ በሴቶች መብቶች ላይ የሚሰሩ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ይናገራሉ፡፡


እነዚሁ ድርጅቶችም ክፍተት አሉባቸው ያሏቸው ህጎች እንዲስተካከሉ ስራዎችን እየከወኑ መሆኑን ሲናገሩ ሰምተናል፡፡


ፋሲካ ሙሉወርቅ



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…



Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page