top of page

በህክምናው ዘርፍ የምርምር ስራዎችን የማስፋፋት ስራ

  • Jun 23
  • 1 min read

ሰኔ 16/2018


በህክምናው ዘርፍ የምርምር ስራዎችን ማስፋፋት ለሀገራት የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ስራ ላይ አስተዋጽኦ እንዳለው ይነገራል፡፡


ተላላፊ እንዲሁም ተላላፊ ባልሆኑ ህመሞች የህክምና መላ ላይ ዘመናዊ የምርምር ላብራቶሪዎችን በመገንባት ከዚህ ቀደም ብዙ ወጪ እና ጊዜ ይጠይቁ የነበሩ ምርምሮች እዚሁ በሀገር ቤት እየተደረጉ ነው ተብሏል፡፡


ለተለያዩ ህመሞች መፈወሻ የሚመረቱ መድሀኒቶች ጥቅም ላይ ከመዋላቸው በፊት የህክምና ሙከራ ለማድረግ እንዲሁም እንደ ካንሰር ያሉ ህመሞች ሳይሰራጩ በፊት ቀድሞ ዓይነታቸውን በምርመራ ለማወቅ የሚያግዙ አሰራሮች መጀመሩን የአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት ተናግሯል፡፡



ከህክምና የሙከራ ጥናቶች ውስጥም ለድንገተኛ ወረርሽኞች በአጭር ጊዜ ተመርተው ለሌሎች ሀገራት የሚሰራጩ መድኃኒቶች በኢትዮጵያ ጥቅም ላይ ከመዋላቸው በፊት የክሊኒካል ሙከራ የሚካሄድበት ስራ እንደሚከውን የአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ዶክተር ዓለምሰገድ አብዲሳ ተናግረዋል፡፡


በሌላ በኩል በኢትዮጵያ ትልቁ የጤና ስጋት የሆነውን የወባ በሽታ ለመከላከል የክትባት ምርት ላይ የተጀመሩ ስራዎች መኖራቸውን የሚጠቅሱት ዶክተር አለምሰገድ የዓለማቀፍ ድጋፎች መቀነስን ተከትሎ እንደ ክትባት ያሉ የህክምና ግብዓቶችን እዚሁ ማምረት ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ጠቅሰዋል፡፡


በተጨማሪም በቅድመ መከላከልና የህመሙን ዓይነት ለይቶ በማወቅ ውጤት የሚገኝበትን የካንሰር ቅድመ ምርመራ ላይ ኢንስቲትዩት የካንሰር ህክምና ከሚሰጡ ተቋማት ጋር እየሰራ ነው ተብሏል፡፡


በጤናው ዘርፍ የሚደረጉ የተለያዩ ምርምሮችና ጥናቶች የህክምና አገልግሎትን ጥራት ለማሻሻል የተሻሻሉ የህክምና አማራጮችን ለመጠቀም እና በማስረጃ ላይ የተመሰረቱ የጤና ፖሊሲዎችን ለማሰናት እንደሚያግዙ ተነግሯል፡፡


በተጨማሪም እንደወረርሽኝ ያሉ ድንገተኛ የጤና ስጋቶችን ቀድሞ ለመከላከልና ለማከም የሚያግዙ በመሆኑም ስራው በሌሎች የምርምር ተቋማትም ላይ መስፋፋት አለበት ተብሏል።


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….


ምህረት ስዩም


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page