በሀይማኖት ተቋማት እና በንጹሃን ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ አወገዘ፡፡
ችግሮች በንግግር እንዲፈቱም ጥሪ አቅርቧል፡፡
‘’ንጹሀን የፖለቲካ ማወራረጃ ሊሆኑ አይገባም’’ ያለው ጉባኤው ‘’ተገቢ የሆነ ጥበቃ እና ከለላ ሊደረግላቸው ይገባል’’ ሲልም ተናግሯል፡፡
አሁን ላይ በየእምነት ተቋማት እና በንጹሀን ላይ የሚደርሰውን ሞትና ጉዳት ‘’ኢ ፍትሃዊ ነው’’ ብሎታል፡፡
የኢትዮጵያ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ፀሀፊ ቀሲስ ታጋይ ታደለ ‘’ሁሉም በየእራሱ መንገድ መሄዱ፣ በመደማመጥና በመነጋገር የሚያምኑ ጥቂቶች መሆናቸው፤ ግጭቶች ጎልተው እንዲታዩ ካደረጉ ምክንያቶች መካከል ናቸው’’ ሲሉ ለሸገር ተናግረዋል፡፡
ማርታ በቀለ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments