top of page

ቅምት 27፣2016 - በኢትዮጵያየአህያ ቄራ እና የአህዮቹ መመናመንም በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ የማህበረሰብ ጫና በእጅጉ እንደሚያበረታው ተነግሯል


በኢትዮጵያበመንግስት ዕውቅና ተሰጥቶት ስራ የጀመረው የአሰላ የአህያ ቄራ ምንም እንኳን ለውጭ ገበያ ታስቦ ቢከፈትም ከቅርብ ጊዜ ወዲህም በአሰላ አካባቢ ያሉ ስጋ ቤቶችም ስጋውን ለሽያጭ ሲያቀርቡ እንደተገኙ ብሩክ ኢትዮጵያ የተሰኘ የአህያ መብት ተሟጋች ተቋም ተናገረ፡፡


በአህያቆዳ ንግድ ምክንያትም በኢትዮጵያ አህዮች ላይ ከፍተኛ የሆነ መመናመን እየታየ ነው ተብሏል።


የአህያቆዳ ንግዱ በዚሁ ከቀጠለም በዓመታት ውስጥ በአለም አቀፍ ደረጃ ዝርያቸው ሊጠፋ እንደሚችል ተነግሯል።


ይህንያለው የአህያ መብት ተሟጋቹ ብሩክ ኢትዮጵያ ነው።


ምንምእንኳን ኢትዮጵያ የአህያ ቁጥሯ ከፍ ያለ ቢሆንም የአህያ ቆዳ ንግዱ በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ ግን እንደሌሎቹ የአለም ሀገራት መመናመናቸው የማይቀር ነው ሲሉ የብሩክ ኢትዮጵያ ዳይሬክተር አቶ ዩሀንስ ቃሲም ተናግረዋል።


በሀገርአቀፍ ደረጃ በመንግስት እውቅና የተሰጠው የአሰላ የአህያ ቄራ አለ ያሉት ዳይሬክተሩ በቀን ከ100 እሰከ 300 አህዮች ለእርድ እንደሚቀርቡ ተናግረዋል።


በዚህየተነሳም ከዚህ ቀደም ከ2,000 እስከ 3,000 ብር ይሸጥ የነበረው አህያ አሁን ከ9,000 እስከ 11,000 ብር እየተሸጠ እንደሆነ ተነግሯል።


በተጨማሪምአህያ ቶሎ ቶሎ አለመራባቷም ችግሩን ያከብደዋል ተብሏል።

በተለይበገጠሩ የሀገሪቱ ክፍል ያሉ ነዋሪዎች በእለት ተእለት ኑሮአቸው ላይ ያለውን አብዛኛውን የጉልበት ስራ የሚከውኑት የጋማ ከብቶች ናቸው የተባለ ሲሆን በብዛት የሚያገለግሉት ግን አህዮች መሆናቸው ተነግሯል።


በዚህምሀገሪቱ ያላት የአህያ ብዛት 10.8 ሚሊዮን ደርሷል ተብሏል፡፡


በኢትዮጵያየአህያ ቄራ መኖር እና የአህዮቹ መመናመንም በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ የገጠሩን ማህበረሰብ ጫና በእጅጉ እንደሚያበረታው ተነግሯል።


ቻይናየባህል መድሀኒት እና የመዋቢያ እቃዎች ለማዘጋጀት ከሚያስፈልጋት ግብአት አንዱ የአህያ ቆዳ በመሆኑ ያሏትን አህዮች ጨርሳ ወደ ሌሎች ሀገራት እያማተረች መሆኑን የተናገሩት ደግሞ በብሩክ ኢትዮጵያ የፕሮግራም አፈፃፀም እና የአቅም ማጎልበት ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ቴዎድሮስ ተስፋዬ ኢትዮጵያም የአህያ ቆዳን በብዛት የምትልከው ወደ ቻይና መሆኑን ተናግረዋል።


ከቆዳቸውምባለፈ ስጋቸው ወደ ውጭ ሀገራት እንደሚላክ ተናግረዋል፡፡


ብሩክኢትዮጵያ በ2006 ዓ.ም ስራ የጀመረ ሲሆን በአለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ በ11 ሀገሮች ላይ እንደሚሰራም ሰምተናል።ፋሲካ ሙሉወርቅየሸገርንወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqzΣχόλια


bottom of page