top of page

ስታንዳርድ ኢንሹራንስ አ.ማ፤ በኢትዮጵያ 19ኛው የመድህን ሰጪ በመሆን ከቀናት በኋላ ገበያውን ይቀላቀላል ተባለ።

  • sheger1021fm
  • Nov 25, 2025
  • 1 min read

ህዳር 16 2018


ስታንዳርድ ኢንሹራንስ አ.ማ፤ በኢትዮጵያ 19ኛው የመድህን ሰጪ በመሆን ከቀናት በኋላ ገበያውን ይቀላቀላል ተባለ።


ኢትዮጵያ የኢንሹራንስ ሽፋን ካላደገባቸው እና በኢኮኖሚው ውስጥ ያለው ድርሻም ዝቅተኛ ከሆነባቸው ከቀዳሚ ሀገሮች ውስጥ መሆኗ ይነገራል።


''በኢትዮጵያ የኢንሹራንስ ሽፋን ገና ያልደረሰባቸው ብዙ የስራ ዘርፎች አሉ'' ሲሉ የስታንዳርድ ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና ሰራ አስፈፃሚ አቶ ሰለሞን አሰፋ ነግረውናል።


ከ305 ሚሊየን ብር በላይ ካፒታል በማስመዝገብ ከብሔራዊ ባንክ እውቅና በማግኘት 19ኛው የኢንሹራንስ ሰጪ ኩባንያ በመሆን ስራ የሚጀምረው ስታንዳርድ ኢንሹራንስ፤ የአዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበር 1747 አባላት የመሰረቱት መሆኑን ዋና ስራ አስፈፃሚው ነግረውናል።

የኢንሹራንስ ተቋሙ ትልቁ ባለድርሻም አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበር ነው ተብሏል።


በሳምንቱ መጨረሻም የኢንሹራንስ ተቋሙ እና የኅብረት ስራ ማህበሩ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።


ዋና ሰራ አስፈፃሚው አቶ ሰለሞን፣ ስምምነቱ አዋጭ ለሚሰጠው የብድር አገልግሎት ስታንዳርድ ኢንሹራንስ የመድህን ሽፋን ለመስጠት እንዲችል ለማድረግ በማሰብ የተፈረመ ነው ብለውናል።


ከሁለት ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ስራ ይጀምራል የተባለው ስታንዳርድ ኢንሹራንስ፣ የጠቅላላ (General) እና የህይወት(life) ኢንሹራንስ አገልግሎትን በመስጠት ስራውን ይጀምራል ተብሏል።


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…


ቴዎድሮስ ወርቁ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page