top of page

ሰኔ 8፣ 2016 - ኢትዮጵያ 150 ጊጋ ዋት በላይ እምቅ የኢነርጂ ሀይል ቢኖራትም፤ እስካሁን የመነጨው ሀይል ግን 5.4 ጊጋ ዋት ብቻ ነው ተባለ፡፡

ኢትዮጵያ 150 ጊጋ ዋት በላይ እምቅ የኢነርጂ ሀይል ቢኖራትም፤ እስካሁን የመነጨው ሀይል ግን 5.4 ጊጋ ዋት ብቻ ነው ተባለ፡፡


ይህን ያሉት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ኢንጂነር ሱልጣን ዋሌ(ዶ/ር) ናቸው፡፡


ሚኒስትር ድኤታው ምክንያታዊው የናይል ወንዝ አጠቃቀምና ቀጠናዊ ውህደት ዓመታዊ ፎረም ላይ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያ ያላትን የሀይል እምቅ ሀብት መጠቀም ያልቻለችው መስኩ በጣም ከፍተኛ የሆነ መዋዕለ ነዋይ የሚጠይቅ በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡


ዛሬ በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል የአባይ ተፋሰስ ሀገራት የውሃ ሀብትን በጋራ እና በፍትሃዊነት መጠቀም ስለሚችሉባቸው መንገዶች ላይ የሚመክሩበት የ’’አፍሪ ራን’’ ሶስተኛው ጉባኤ እየተካሄደ ነው፡፡

የጉባኤው አላማን የተመለከተ ሚኒስትር ድኤታ ኢንጅነር ሱልጣን ዋሌ፤ በዋናነት 14 ዓመት የሞላውን የኮፕሬሲፍ ፍሬም ወርክ ስምምነት የት እንደደረሰ ለመገምገም ያለመ ነው ብለዋል፡፡


ስምምነቱ የውሃ አጠቃቀም እና አስተዳደር ላይ የሚመለከቱ ጉዳዮችን ያቀፈ ሰነድ መሆኑ አስረድተዋል፡፡


ሌላው አላማው የሀይል ትስስር ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ይህም ቀጠናውን በሀይል ለማስተሳሰር ያለመ ነው ያሉ ሲሆን ከፍተኛ ያለመረጋጋት የሚታይበትን የተፋሰሱን ሀገራት በሀይል ለማስተሳሰር የሚያስችል ውይይት ይደረግበታል ብለዋል፡፡


እስካሁንም ኢትዮጵያ፤ ለ10 ዓመት ያክል ለጅቡቲ፣ ለ8 ዓመት ያክል ለሱዳን፣ ለኬኒያ ላለፉት 2 ዓመታት ኤሌክትሪክ ሀይል እያቀረበች ነው፡፡


ኢትዮጵያ ከምስራቅ አፍሪካ ብቸኛዋ ያውም በዝቅተኛ ኤሌክትሪክ ታሪክ፤ ሀይል እያቀረበች ያለች ሀገር ነች ሲሉ ሚኒስትር ድኤታው አስረድተዋል፡፡


ሶስተኛው ደግሞ ታላቁ ህዳሴ ግድቡን ለልማትና ለትስስር እንዴት እንጠቀም በሚል ጉዳይ ላይ ጉባኤው ይመክራል ብለዋል፡፡


ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page