የኢትዮጵያ ኃይል አቅራቢ ተቋማት ‘’አሁን ያለው የኤሌክትሪክ ሽያጭ ታሪፍ ማሻሻያ ካልተደረገበት ከገባንበት ኪሳራ ይበልጥ ለቀውስ የሚያጋልጠን ነው’’ አሉ፡፡
ይህ የተባለው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሀይል ሽያጭ ታሪፍ ይጨመርልን የሚል ጥያቄ በሰነድ አስደግፈው ለነዳጅ እና ኢነርጅ ባለስልጣን ባቀረቡት ረቂቅ ሰነድ ላይ ነው፡፡
ኤሌክትሪክ ሽያጭ የተሰበሰበ ያለው ገቢ ወጪን መሸፈን የማይችል ነው ሲሉ ተቋማቱ ባቀረቡት ጥናት ላይ ተናግረዋል፡፡
በዚህ እና በሌሎች ምክንያቶችም ኪሳራ ውስጥ እየገባን ነው ብለዋል፡፡
Comentários