በኢትዮጵያ አሁን ያለው ጦርነት፣ ስራ አጥነት፣ መፈናቀል፣ ረሀብ እና ሱስ የአዕምሮ ህመም ታማሚዎች ቁጥርን ከፍ እየደረጉት እንደሆነ ተገምቷል፡፡
የአዕምሮ ህመም ከህመምነቱ በተጨማሪ የብዙ ኢትዮጵያዊያንን ምጣኔ ሐብትም እያቃወሰ ነው ተብሏል፡፡
በጥናት ተደግፎ ይህን ያህል ሊባል ባይቻልም፤ በኢትዮጵያ የአዕምሮ ህመም ያለባቸው ሰዎች ብዙ እንደሆኑ ይነገራል፡፡
ህመሙ ከታማሚዎቹ በተጨማሪ የቤተሰቦቻቸው ብሎም የሀገርን ኢኮኖሚ እጅጉን እየፈተነው እንዳለ ተነግሯል፡፡
በአሁኑ ወቅትም በተለይ አምራች የሚባለው ወጣቱ ሀይል በህመሙ እየተጠቃ እንደሆነና ይህም እንደ ሀገር የሚያሳጣው ቀላል የማይባል መሆኑን የዘርፉ ባለሞያዎች ለሸገር ነግረዋል፡፡
በአዕምሮ ህመም ዙሪያ በርካታ ጥናቶችን ያደረጉት ፕ/ር አታላይ አለም፤ እንደሀገር ጉዳዩ አሳሳቢ እንደሆ እና በተለይም የአዕምሮ ህመም የታመመው ሰው የቤተሰብ አስተዳዳሪ ከነበረ በሌሎች ላይ የሚያደርሰው ጉዳት እንደሚያከፋውም ያስረዳሉ፡፡
በዚህ ወቅት በዓለም ዙሪያ በአማካኝ ከ 8 ሰዎች መካከል አንደኛው የአእምሮ ህመም ተጠቂ እንደሆነም ጥናት አሳይቷል፡፡
በጥናት ተደርሶባቸዋል የተባሉ የአእምሮ ህመም አይነቶች ደግሞ 300 ገደማ ናቸው ተብሏል፡፡
በኢትዮጵያ በዚህ ጊዜ የሰለጠኑ የአዕምሮ ህመም ሀኪሞች በቁጥር 150 ብቻ እንደሆኑም ሰምተናል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ…
ማንያዘዋል ጌታሁን
댓글