top of page

ሰኔ 7፣ 2016 - ልማት ባንክ ባለፉት 3 ዓመታት ለግብርናው ዘርፍ ከሰጠው 10 ቢሊዮን ብር ብድር፤ ግማሹ የተበላሸ ብድር ሆኗል ተባለ

ልማት ባንክ ባለፉት 3 ዓመታት ለግብርናው ዘርፍ ከሰጠው 10 ቢሊዮን ብር ብድር፤ ግማሹ የተበላሸ ብድር ሆኗል ተባለ፡፡

 

ባንኩ ብድር ሲሰጥ ከባለሀብቶች እንደ መያዣ ይዞት ከነበረው መሬት 35 ሺህ ሄክታሩንም በክልሎች አፅድቄአለሁ ብሏል፡፡

 

ልማት ባንክ ለግብርናው ዘርፍ ባለፉት 11 ወራት 7.1 ቢልየን ብር ብድር ማፅደቁን ተናግሯል።

 

ከፀደቅው ብድር ውስጥ 1.9 ቢልየን ብሩ ለሰፋፊ እርሻዎች ነው የተሰጠው ሲሉ የባንኩ ፕሬዝዳንት ዮሀንስ አያሌው (ዶ/ር) ተናግረዋል።

 

ልማት ባንክ አምና ለግብርነው ዘርፍ 3.4 ቢልየን ብር ብድር ሰጥቶ ነበር የተባለ ሲሆን ባንኩ ከጊዜ ወደ ጊዜ ለግብርናው ዘርፍ የሚሰጠው ብድር እየጨመረ መጥቷል ተብሏል።

 

ልማት ባንክ ለግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ ብድሮች ሲሰጥ ወለዱ 7 በመቶ ነው ያሉት ዶክተር ዮሀንስ ይህም ባንኩ ከሚበደርበት 2 ከመቶ በመቀነስ ለዘርፉ ብድሮችን እያቀረበ ነው ብለዋል።

 

የግብርና ሚንስትር ዴዕታ ሶፍያ አያሌው በበኩላቸው፤ አሁን ላይ 5755 ባለሀብቶች በግብርናው ዘርፍ ኢንቨስት እያደረጉ ነው ከዚህ ውስጥ 5674 የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን ናቸው ብለዋል።

 

ሚንስትር ዴዕታዋ ለባለሀብቶች 2. 2 ሚሊየን ሄክታር መሬት የተላለፈ ቢሆንም እስካሁ ወደ ስራ የገባው 41 ከመቶ ብቻ ነው ይላሉ።

 

59 ከመቶ የሚሆነው መሬት ለባለሀብቱ ቢተላለፍም እስካሁን እያለሙት አይደለም ያሉት ዳክተር ሶፍያ ይህንን ለማስተካከል በቅርበት ክልሎችና የግብርና ሚኒስቴር በጋራ ይሰራሉ።

 

በየጊዜው የመሰረተ ልማት አቅርቦት መሬት በፍጥነት አለማስተላለፍ ና ዝግጅት የብድር አቅርቦትና ሌሎችም ችግሮች በግብርናው ዘርፍ የተሰማራው ባለሀብት ወደስራ እንዳይገባና ስራቸውን በስፋት እንዳይሰራ አድርጓቸዋል ተብሏል።

 

በሌላ በኩል ባለሀብቱ መሬት ከመውሰዱ በፊት አካባቢው ላይ ምን መመረት እንዳለበት ጥናት ማድረግ አለበት ያሉት ሚንስትር ዴዕታዋ አንዳንድ ክልሎች ላይ ባለሀብቱ ጥናት ሳያደርግ እየገባ በአካባቢው የማይበቅሉ ሰብሎች ለማልማት ሲጥር ይስተዋላል ብለዋል።

 

የግብርና ሚንስቴር የግብርናው ዘርፍ የበለጠ ለማዘመን ባለሀብቶች፣ በዘርፉ ኢንቨስት እንዲያደርጉ እያበረታታ ነው ተብሏል።

 

የኢትዮጵያ የወጪ ምርት ከ65 እስከ 70 ከመቶ የሚሆነው ገቢ የሚገኘው ከግብርናው ዘርፍ መሆኑ ይነገራል፡፡

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page