top of page

ሰኔ 6 2017 - አዲሱ የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ረቂቅ አዋጅ አስገዳጅ የትምህርት ደረጃን አያስቀምጥም

  • sheger1021fm
  • Jun 13
  • 1 min read

አዲሱ የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ረቂቅ አዋጅ አስገዳጅ የትምህርት ደረጃን አያስቀምጥም


በስራ ላይ ያለው አዋጅ ግን ቢያንስ 8ኛ ክፍልን አስገዳጅ ያደረገ ነበር ተብሏል፡፡


በትናንትናው ዕለት ፓርላማው ለሰው ሃብት ልማት፣ ስራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የመራው ረቂቅ አዋጅ ‘’በባህርተኞች እና በቤት ሰራተኞች ላይ ነው ትኩረት ያደረገው’’ የሚል ትችት ከምክር ቤት አባላት የቀረበበት ሲሆን ከመጽደቁ በፊት በሌሎች የትምህርት መስኮች የተማሩ ኢትዮጵያንን እንዲካትት ተጠይቋል፡፡


የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ረቂቅ አዋጅ፤ አንድ ግለሰብ ኤጀንሲ ለመክፈት ፍላጎት ቢኖረው የግድ ኢትዮጵያዊ መሆን እንዳለበት የሚደነግግ ሲሆን የሚስፈልገው ካፒታል በተመለከተ ደግሞ፤


ለደረጃ አንድ 20 ሚሊዮን፣


ለደረጃ ሁለት 15 ሚሊዮን፣


ለደረጃ ሶስት 10 ሚሊዮን፣


ለደረጃ አራት 7.5 ሚሊዮን ብር ካፒታል እንዲኖራቸው ተብሏል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… https://www.mixcloud.com/ShegerFM/tyj/


ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…





Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page