top of page

ሰኔ 6፣ 2016 - ከዓለም አጠቃላይ ህዝብ 1 ቢሊዮን የሚያህለው በተለያዩ የአእምሮ ህመም ተጠቂ ሆኗል፡፡

ከዓለም አጠቃላይ ህዝብ 1 ቢሊዮን የሚያህለው በተለያዩ የአእምሮ ህመም ተጠቂ ሆኗል፡፡


እንደ ኢትዮጵያ ያሉ አነስተኛ  ገቢ ያላቸው ሀገራት ዜጎች ደግሞ የበለጠ  ተጠቂ ሆነዋል፡፡


ይኽንን የተናገሩት፣ በአዕምሮ ህመም ላይ በርካታ ጥናቶችን ያደረጉት ኘ/ር አታላይ ዓለም፤ የአማኑኤል ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተሀድሶ ህክምናን በተመለከተ ባዘጋጀው መድረክ ላይ ነው።



1 ቢሊዮን የሚያህለው የአለም ሕዝብ፤ በቁጥር 300 በሚሆኑ የአዕምሮ ሕመም ችግሮች ውስጥ እንደሚገኝ በጥናት መረጋገጡ ተጠቅሷል፡፡


በኢትዮጵያ ይህንን የአእምሮ ህመም የሚያደርሰው ማህበራዊ ቀውስን ለመቀነስ ''የተሀድሶ ህክምና'' ላይ መስራት ቢያስፈልግም ግን ስለ ተሀድሶ ህክምና በኢትዮጵያ ያለው ግንዛቤም ደካማ መሆኑን ፕሮፌሰር አታላይ ተናግረዋል፡፡ 


የአእምሮ ህመም  ያለባቸው ሰዎች፣ ከሌላው ሰው በአማካኝ ከ10 እስከ 20 ዓመት ቀድመው የመሞት እድል እንዳላቸውና ራሳቸውን ከሚያጠፉ 10 ሰዎች መካከል በአማካይ 9ኙ የአዕምሮ ህመም ያለባቸው ሆነው እንደሚገኙ ጥናቱ ማሳየቱ ተነግሯል።


ማንያዘዋል ጌታሁን


Comments


bottom of page