ሰኔ 6፣ 2016 - ኢትዮጵያ የግብርና ምርቶችን በግብአትነት ለሚጠቀሙ ኢንዱስትሪዎች ትኩረት ብትሰጥ ያላትን ተወዳዳሪነትም እንደምታሻሽል ባለሞያ ተናገሩ
- sheger1021fm
- Jun 13, 2024
- 1 min read
ኢትዮጵያ የግብርና ምርቶችን በግብአትነት ለሚጠቀሙ ኢንዱስትሪዎች ትኩረት ብትሰጥ በአለም ገበያ ያላትን ተወዳዳሪነትም እንደምታሻሽል ባለሞያ ተናገሩ።
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የተመሰረተው ግብርና ላይ በመሆኑ ኢንዱስትሪዎች በዚሁ ላይ ቢያተኩሩ የተሻለ ነው ተብሎዋል፡፡
80 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ አርሶ አደር በመሆኑ ጠቀሜታው የጎላ ነው የተባለ ሲሆን፤ ለኢንዱስትሪው ትልቁን ግብአት የሚያቀርበው ግብርናው እንደሆነም ባለሞያው ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ግብርና መር ኢንዱስትሪን እንደምትከተል እና አሁን ላይ ግን ሁሉንም አካታች ዘርፍ እንደምትከተል ሰምተናል፡፡
በሀገር ውስጥ በቂ የሆነ የግብርና ምርት ካለ ከውጭ ጥሬ ዕቃ አምጥቶ ማምረት አዋጭ እንዳልሆነ ባለሞያው ለሸገር ተናግረዋል፡፡
Commenti