top of page

ሰኔ 5 2017 - ቴክኖሎጂን ተጠቅመው በትምህርት ላይ መፍትሔ ያመጡ ስራ ፈጣሪዎች ከፋይናንስ ተቋማት ፣ከቴክኖሎጂ አቅራቢዎች እና ሌሎች ተቋማትና ግለሰቦች ጋር የተገናኙበት መድረክ ከትላንት ጀምሮ በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄ ነው።

  • sheger1021fm
  • Jun 12
  • 1 min read

በዚህ ዝግጅት ላይ ለትምህርት በቴክኖሎጂ የታገዘ መፍትሔ ይዘው የቀረቡ 11 ስራ ፈጣሪዎች ቀርበዋል።


እነዚህ ስራ ፈጣሪዎች "Reach for change" በተባለ አለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅት ለ1 ዓመት ያህል ስልጠና፣ድጋፍ ሲደረግላቸው የቆዩ መሆናቸውን ሰምተናል።


ፕሮግራሙን በገንዘብ የደገፈው ደግሞ ማስተርካርድ ፋውንዴሽን ነው።


ሪች ፎር ጄንጅ የማህበረሰብ ችግሮችን ለመፍታት የተቋቋሙ ስራ ፈጣሪዎችን ያግዛል፣ይደግፋል ሲሉ የድርጅቱ የኢትዮጵያ ሀላፊ  መቅድም ጉልላት ተናግረዋል።


በዚህ "MasterCard Foundation Ed _Tech fellowship Program " 3 ቡድኖች መኖራቸውን የጠቀሱት ሀላፊዋ የመጀመሪያዎቹ የእድሉ ተጠቃሚዎች የሆኑ 11 ስራ ፈጣሪዎች ለ1 ዓመት ስልጠና ወስደዋል፣ስራቸውን የሚያሳድጉበትም ለእያንዳንዳቸው 60000 ዶላር ተሰጥቷቸዋል ብለዋል።


በሸራተን አዲስ ሆቴል ትናንት በጀመረውና ዛሬም በሚቀጥለው ፕሮግራም ላይ ስራ ፈጣሪዎቹ ከፋይናንስ ተቋማት፣ከባለ ሙዓለ ነዋዮች ጋር ትስስር የሚፈጥሩበት መድረክ ነው ተብሏል።


ንጋቱ ሙሉ


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ...👇👇👇👇👇👇👇👇👇


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page