top of page

ሰኔ 4 2017 - መንግስት የነዳጅ ሽያጭ ላይ 15 በመቶ የተጨማሪ እሴት ታክስ ማስከፈል ሊጀምር ነው፡፡

  • sheger1021fm
  • Jun 11
  • 1 min read

ከመጭው ሐምሌ ወር ጀምሮ የነዳጅ ግብይትን በአለም አቀፉ ዋጋ መሰረት ይሆናል ተብሎም ይጠበቃል፡፡


ላለፉት ወራት ቀስ በቀስ የነዳጅ ድጎማን እያነሳ ያለው መንግስት ሙሉ በሙሉ ድጎማውን ከማቆም ባሻገር ተጨማሪ እሴት ታክስ ሊያስከፍልበት ማቀዱ ተሰምቷል፡፡


የፌዴራል መንግስት የ2018 ረቂቅ በጀት እንደሚያሳየው ከነዳጅና የነዳጅ ውጤቶች 15 በመቶ ቫት በማስከፈል ከ3 ቢሊየን ብር በላይ ለመሰብሰብ ማቀዱን ያሳያል፡፡


የፌዴራል መንግስት የ2018 የገቢ በጀት በሚል ለፓርላማው የቀረበው ረቂቅ በጀት ከስኳርም 1 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር እና ከጨው 337 ሚሊየን ብር ተጨማሪ እሴት ታክስ ለመሰብሰብ መታቀዱን ያሳያል፡፡


ከዚህ ቀደም እንደ ዘይት እና ስኳር ያሉ ምርቶች በመንግስት የሚደጎሙና ዋጋቸውም ተመጣጣኝ እንዲሆን ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ የነበሩ መሆናቸው አይዘነጋም፡፡


ትዕግስት ዘሪሁን

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page