top of page

ሰኔ 4፣ 2016 - የዋጋ ንረቱ በመጪው ዓመትም ባለሁት አሃዝ ሆኖ እንደሚቀጥል ተተነበየ

የዋጋ ንረቱ በመጪው ዓመትም ባለሁት አሃዝ ሆኖ እንደሚቀጥል ተተነበየ፡፡


በመጪው ዓመት አጠቃላይ የዋጋ ንረቱ 12 በመቶ እንደሚሆን የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል፡፡


የፍጆታ እቃዎች እና የአገልግሎት የዋጋ እድገት፤ እየተገባደደ ባለው የበጀት ዓመት የመቀነስ አዝማሚያ እያሳየ ቢሆንም ባለሁለት አሃዝ ሆኖ እንደሚቀጥል መገመቱን ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ተናግረዋል፡፡

ግሽበቱ በግንቦት ወር መጨረሻ ከነበረበት 27.4 በመቶ በመጭው ዓመት ወደ 12 በመቶ ዝቅ እንዲል ለማስቻልም ጥብቅ የገንዘብ እና ፊሲካል ፖሊሲ እርምጃዎች ይወሰዳሉ ብለዋል ሚኒስትሩ፡፡


የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ የ2017 አመትን የመንግስት ረቂቅ በጀት ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ሲያቀርቡ ነው ይሄንን ያሉት፡፡

Comments


bottom of page