top of page

ሰኔ 4፣ 2016 - የአካል ጉዳተኞች በሀገራዊ ምክከሩ ጉዳያቸዉ እንዲደመጥ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጠየቀ፡፡

የአካል ጉዳተኞች በሀገራዊ ምክከሩ ጉዳያቸዉ እንዲደመጥ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጠየቀ፡፡


ኢትዮጵያ በምታካሄደው አገራዊ ምክክር ላይ የአከል ጉዳተኞች ጥያቄዎች እንዲደመጡም መፍትሄም እንዲያገኙ ኢሰመኮ ጠይቋል፡፡


አካል ጉዳተኞች በምክክሩ ላይ ትርጉም ያለዉ ተሳትፎ እንዲያደርጉ አፈልጋለሁ ሲል ኮሚሽኑ አስረድቷል፡፡


በኮሚሽኑ የሴቶች የህጻናት የአረጋውያን እና የአክል ጉዳተኞች መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገብረሐዋሪያ፤ በሰጡት ምክረ ሀሳብ የአካል ጉዳተኞችን ተሳትፎ ማረጋገጥ ከመንግስት ይጠበቃል፤ በምክከሩ መሳተፍ ደግም የአካል ጉዳተኞች መብት ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡


የአካል ጉዳተኞች በማህበራቸው እና በተወካዮቻቸው በኩል መፍትሄ ያስፈልገዋል ያሉትን ጉዳይ ለምክክሩ እንዲቀርቡም ተጠይቀዋል፡፡


ኮሚሽነር ርግበ ከግጭት እና ጦርነት ጋር የተያያዙ ጉዳይዎችም ሆኑ ከግጭት አዉድ ዉጭ የሆኑ አካል ጉዳተረኖች እንዲመለሱላቸዉ የሚፈልጉትን ጥያቄዎች በአግባቡ ከተወከሉና ትርጉም ባለዉ መልኩ ከተሳተፉ ጥያቄዎቸቻቸዉ አጀንዳ ሊሆንላቸዉ እንደሚችል አስረድተዋል፡፡


የአካል ጉዳተኞችን ተሳትፎ የምናረጋግጠዉ ጥያቄዎቻቸዉ በአጃንዳዎች ዉስጥ በመካተታቸዉ ነዉም ብሏል ኮሚሽኑ፡፡


የአካል ጉዳተኞች መሃበራት እና አካል ጉዳተኞች ላይ የሚሰሩ ድርጅቶች ከምክክር ኮሚሽኑ ጋር በቅርበት እንዲሰሩም ተጠይቋል፡፡


ያሬድ እንዳሻው



Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page