ኢትዮጵያ በአፍሪካ በቁም እንስሳት ሀብቷ ቀዳሚ ሀገር መሆኗ በተለያዮ ሰነዶች ይጠቀሳል፡፡
የግብርና ሚኒስቴር ባወጣው መረጃ መሰረት ኢትዮጵያ አሁን ላይ ከ 200 ሚልዮን በላይ የቁም እንስሳት አላት፡፡
ነገር ግን ከዚህ ውስጥ እስካሁን ወደ ውጭ በመላክ ገቢ የምታገኝበት ቁጥር መረጃው በጣም ዝቅተኛ ነው፡፡
በዚህ ዓመት እንኳን ኢትዮጵያ ወደ ውጭ የላከችው የቁም እንስሳት ምርት 250 ሺህ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የእንስሳት ኳራንታይን እና ሬጉራቶሪ መሪ ስራ አስፈፃሚ ሰይፉ ሀይሉ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ በህጋዊ መንገድ በሳምንት ወደ ውጪ ሀገር የምትልከው የቁም እንስሳት በአማካይ 10 ሺህ ገደማ ብቻ ነው፡፡
በኮንትሮባንድ ንግድ ግን በየቀኑ ከዚህ እጥፍ የሆነ የቁም እንስሳት ወደ ጎረቤት ሀገር ይሄዳሉ ያሉ ሲሆን ይህም ሀገሪቱ ከፍተኛ ገቢ እያሳጣት ነው፡፡
Comments