top of page

ሰኔ 3፣ 2016 - የፀጥታ ችግር የእምቦጭ አረም ትኩረት እንዲያጣ አድርጎታል ተባለ

  • sheger1021fm
  • Jun 10, 2024
  • 1 min read

ለተለያዩ አካባቢዎች ያለው የፀጥታ ችግር የእምቦጭ አረም ትኩረት እንዲያጣ አድርጎታል ተባለ፡፡


አረሙም በሀይቆች እና ግድቦች ላይ አደጋን እንደደቀነ ቀጥሏል፡፡


ይህ የሆነው ደግሞ አረሙ ዘሩን ከመበተኑ በፊት ሊደረግ የሚገባው ክትትል በመቀነሱ ነው ተብሏል፡፡


በተለያዩ አካባቢዎች ያለው የሰላም እጦት አረሙ ከመስፋቱ በፊት መቆጣጠር እንዳይቻል አድርጓል የተባለ ሲሆን በጣና ሀይቅ፣ በቆቃ ግድብ ሀይል ማመንጫ፣ ዝዋይ ሀይቅ፣ አበያ ሀይቅ እና በሌሎችም የውሀ አካላት ላይ የእንቦጭ አረም እየተስፋፋ መሆኑንም ሰምተናል፡፡


ኢትዮጵያ ካላት የውሀ አካላት ላይ እስከ 16 ሺህ ሄክታሩ በአረሙ ተሸፍኗል መባሉን የተናገረው የውሃ እና ኢነርጅ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሀ ግድቦች ላይም እየተስፋፋ ነው ብሏል፡፡


#እንቦጭ አረሙ በሰፋበት ልክ እና በጉዳት መጠኑ የተሰጠው ትኩረት ከአረሙ ስፋት ጋር ሲነፃፀር ዝቅተኛ መሆኑን ሸገር ከኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲቱት ሰምቷል፡፡


አረሙ የመስፋፋት አቅሙ በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ እና ትኩረት እንደተነፈገው ከቀጠለ ለህዳሴ ግድቡ አስጊ መሆኑ ተነግሮለታል፡፡


እንቦጭ አረም እያደረሰ ያለውን ጉዳት እንዴት መቀነስ ይቻላል?


ወደፊትስ እንዳይከሰት ምን ማድረግ አለብን የሚለው ጉዳይ ላይ የውሃ እና ኢነርጅ ሚኒስቴር መክሮ ስራዎችን መከወን መጀመሩን ሸገር ሰምቷል፡፡


ፋሲካ ሙሉወርቅ



Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page