top of page

ሰኔ 3፣ 2016 - ብክለት እያስከተለ ያለውን ችግር ለማስቆም በፍርድ ቤት የሚከራከሩ በጎ ፈቃደኛ ባለሙያዎች በመንግስት የስራ ሀላፊዎች ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው ነው ተባለ

የአካባቢ ብክለት እያስከተለ ያለውን ችግር ለማስቆም ህዝብን ወክለው በፍርድ ቤት የሚከራከሩ በጎ ፈቃደኛ የህግ ባለሙያዎች በመንግስት የስራ ሀላፊዎች ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው ነው ተባለ፡፡


የአካባቢ ብክለትን ለመቆጣጠርና ለመከላከል በሚደረግ ስራ ላይ አካባቢን የበከሉ የመንግስት ተቋማትንና ፋብሪካዎችን ተጠያቂ ለማድረግ ህዝብን ወክለው በፍርድ ቤት የሚከራከሩ የህግ ባለሞያዎች ላይ ከፍተኛ ዛቻና ማስፈራራት እየደረሰባቸው መሆኑን በአካባቢ ጥበቃ ላይ የሚሰራው ቁም ለአካባቢ የተሰኘው መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ተናግሯል።


በድርጅቱ ውስጥ በበጎ ፈቃድ የሚሰሩ የህግ ባለሙያዎች በሚደርስባቸው ዛቻ እና ማስፈራራት ምክንያት ለድርጅቱ ህልውና አደጋ መሆኑም ተጠቅሷል።


ይሁን እንጂ የአካባቢ ብክለትን ለመቆጣጠር በሚደረገው ስራና ህብረተሰቡ ነፃ የሆነ አየር የማግኘት መብታቸውን ከማስጠበቅ አኳያ እገዛ የሚያደርጉ የመንግስት ተቋማትና ኃላፊዎች እንዳሉም ተነግሯል ።


ቁም ለአካባቢ የተሰኘው መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በበጎ አድራጊዎች የተመሰረተ ሲሆን በአካባቢ ጉዳይ በርካታ የተጠያቂነት ስራን መስራቱ ይነገራል።


ድርጅቱ አሁን ላይ አሉብኝ ካላቸው ችግሮች ውስጥም የፋይናንስ እጥረት አንዱ መሆኑንም ሰምተናል።



Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page