ሰኔ 28 2017 - "ታላቁ የአፍሪካ ሩጫ" በመጪው ዓመት ጥቅምት ወር ላይ ለማካሄድ ዝግጅቱ መጀመሩ ተሰማ።
- sheger1021fm
- 4 days ago
- 1 min read
በሀገረ አሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን እንዲሁም የሌሎች ሀገር ዜጎች የጎዳና ላይ ሩጫ እንዲሮጡና የባህል ልውውጥ እንዲያደርጉ የሚሰናዳው "ታላቁ የአፍሪካ ሩጫ" በመጪው ዓመት ጥቅምት ወር ላይ ለማካሄድ ዝግጅቱ መጀመሩ ተሰማ።
ኖቫ ኮኔክሽንስ ዘንድሮ ለ7ኛ ጊዜ በሚያዘጋጀው በዚህ "ታላቁ የአፍሪካ ሩጫ" ላይ 5,000 ተሳታፊዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የ5 ኪ.ሜ ሩጫ በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ አሌክሳንድሪያ ጥቅምት 1/2018 ዓ.ም እንደሚካሄድ ተነግሯል።
በውድድሩ ላይ ስመጥር የኢትዮጵያ አትሌቶች፣ ቢዝነስ አቀላጣፊዎች፣ ድምፃዊያን፣ ተዋኒያን ይሳተፋሉ ሲል አዘጋጁ ኖቫ ኮኔክሽንስ በዛሬው እለት በሰጠው መግለጫ ተናግሯል።
በውድድሩ ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ በ www.africanrun.com ድረገፅ ላይ መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል።
በተመሳሳይ ኖቫ ኮኔክሽንስ ተፅኖ ፈጣሪ ሰዎቸን የሚሸልምበትና የሚያጀግንበት ''African Impact Award'' ደግሞ ጥር 2/2018 ዓ.ም እንደሚካሄድ ሰምተናል።

በዚህ ዘርፍ ተፅኖ ፈጣሪ ተብለው ከተሸለሙት መካከል ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን(ቴዲ አፍሮ)አትሌት ደራርቱ ቱሉ፣ ሙዚቀኛ ሙላቱ አስታጥቄ፣ ድምፃዊት አስቴር አወቀ፣ አቶ ግርማ ዋቄ እንዲሁም ጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ ይገኙበታል።
ሁለቱም ዝግጅቶች በተለይ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን በማገናኘት እንዲጫወቱ፣ እንዲዝናኑ መልካም እድል መፍጠራቸው ይነገርላቸዋል።
የባለፉት ዓመታት ዝግጅቶች ከአሌክሳንደሪያና ሞንትጎሞሪ ካውንቲ እውቅና እንደተሰጣቸው እንዲሁም ከዋሽንግተን ዲሳ ሲልቨር ስፕሪንግ እና ሌሎች ከተሞች ከንቲባዎች ድጋፍ ሲያደርጉ መቆየታቸውም ተጠቅሷል።
የ2025 የታላቁ የአፍሪካ ሩጫ እና አፍሪካን ኢምፓክት አዋርድ ምዝገባ መጀመሩ በተነገረበት ዝግጅት ላይ አትሌቶች፣ ተዋናዮች እና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።
ንጋቱ ሙሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments