top of page

ሰኔ 28 2017 - በገቢ ግብር ማሻሽያ አዋጅ ላይ ዝቅተኛ  የግብር ከፋይ መነሻ ደመወዝ 5,000 ብር እንዲሆን በምክር ቤት ተጠየቀ

  • sheger1021fm
  • 4 days ago
  • 2 min read

ይህ ጥያቄ የተጠየቀው የህዝብ እንደራሴዎች ምክርቤት ዛሬ  ከሰዓት በጠራው ልዩ መደበኛ ስብሰባ ላይ ነው፡፡


አሁን በስራ ላይ ያለው የገቢ ግብር አዋጅ ከዘመኑ የኢኮኖሚ ሁኔታ አብሮ እንደማይሄድ እና ከዲጂታል ኢኮኖሚ ጋር እንደማይጣጣም በአዋጁ ላይ በቀረበው አጭር ማብራርያ ተመላክቷል፡፡


የማሻሽያ አዋጁን በተመለከተ ሃሳብ የሰጡት የምክርቤት አባሉ አቶ ባርጠማ ፍቃዱ በአዋጁ አንቅጽ 11 ላይ  የቀድሞው ተሰርዞ አዲስ ሃሳብ እንደገባ ተናግረው ከዚህ በፊት ተቀጣሪ  ከደሞዘ የሚከፍለው ግብር ከ600  ብር በላይ ጀምሮ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡


ተሻሽሎ በቀረበው አዋጅ ግን ከ600 ብር ወደ 2,000 ብር ማደጉን ያሰታወሱት አቶ ባርጠማ ፍቃዱ በመሰረቱ 2 ሺ ብር አሁን በአገራችን የሚቀጠር ሰው የለም ብለዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በመንግስት ተቋም ጽዳት፣የጉልበት ስራ እና የመሳሰሉ ስራዎች ነበሩ ከ600 ብር እስከ 1,000 ብር ደሞዝ አሁን ባለው ሁኔታ ከ4,500 ብር ባለይ ነው ቅጥር ያለው ሲሉ የምክር ቤት አባሉ አሰረድተዋል፡፡


አሁን የ 2,000 ብር ደሞዝ የለም ሲሉ የተናገሩት አቶ ባርጠማ በሌለ ነገር ከዚያ በታች ያለው ነጻ ነው ብንል ታክስ መቀነስ አይደለም ብለዋል፡፡


ቢያንስ እንኳን በቀተኛ ተቀጣሪው ከግብር ነጻ ቢሆን ሲሉ የጠየቁት የምክር ቤት አባሉ ግብር ከፋይዉም ከ5,000 በላይ ያለው ስራተኛ ቢሆን ሲሉ ሃሳባቸውን ሰጥተዋል፡፡


35 በመቶ ግብር እንዲከፍል የተቀመጠው ከ14ሺ 100 በላይ ነው ሲሉ የተናገሩት አቶ ባርጠማ ፍቃዱ ይህም ከወቅቱ ገበያ አንጻር ሲታይ ምንም ነው፤ በዚህ ላይ 35 በመቶ ግብር ሲቆረጥበት ደግሞ በጣም አስቸጋሪ ስለሆነ ወደ 20 ሺ በላይ ከፍ ቢል ሲሉ ሃሳባቸውን አካፍለዋል፡፡


ሌላው የምክርቤት አባሉ በውይቱ ወቅት ሀሳባቸውን የሰጡበት የአዋጁ ክፍል በስራላይ ባለው የግብር መነሻ ላይ ነው፡፡


በስራ ላይ ባለው አዋጅ መነሻ ግብር 10 በመቶ እንደሆነ ተናግረው ተሻሽሎ በቀረበው ረቂቅ አዋጁ ግን 15 በመቶ ብሎ ነው የሚጀምረው ይህም ወደ ቀድሞው ወደ 10 በመቶ ቢመለስ ሲሉ ሃሳባቸው ሰጥተዋል፡፡


የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን በስራ ላይ ባለው አዋጅ ላይ ያለው ከፍተኛ ግብር የሚከፈልበት ደሞዝ በተሸሻለው አዋጅ የዝቅተኛ ግብር መነሻ እንዲሆን መጠየቁን ከዚህ ቀደም መዘገባችን ይታወል።


ኮንፌደሬሽኑ የሰራተኛውን ኑሮ ያገናዘበ የገቢ ግብር ማሻሽያ እንዲደረግም ጠይቆ ነበር፡፡


ዝቅተኛ ገቢ ያለው የህበረተሰብ ክፍል የሚያርፍበትን የግብር ጫና መቀነስ፤ የግብር መሰረትን ማስፋት፤ የግብር ስርአቱ ላይ የሚታዩ የፍትሃዊነት ችግሮችን መቅረፍ፤  የአነስተኛ የንግድ እንቅስቃሴዎች የግብር አከፋፈል ስርአት ቀላል እንዲሆን ማድረግ፤ከአዋጁ አላማዎች ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው ተብሏል፡፡


ምክርቤቱም እነዚህን እና ሌሎች ከአባላት የተነሱ ሃሳቦች ታክለውበት ረቂቅ አዋጁ ለፕላን በጀት እና ፋይናንስ ጉዳይዎች ቋሚ ኮሚቴ በሙሉ ድምጽ መርቶታል፡፡


ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…





Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page