ሰኔ 28 2017 - ሂጅራ ባንክ በዘንድሮው የሂሳብ ዓመት ከ840 ሚሊዮን ብር በላይ ትርፍ አገኘሁ አለ።
- sheger1021fm
- 4 days ago
- 1 min read
ሂጅራ ባንክ በዘንድሮው የሂሳብ ዓመት ከ840 ሚሊዮን ብር በላይ ትርፍ አገኘሁ አለ።
ይህም ውጤት ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ740 በመቶ ጭማሪ አለው ሲል አስረድቷል።
ባንኩ በበጀት ዓመቱ ከ1.8 ቢሊዮን ብር በላይ ጠቅላላ ገቢ መሰብሰቡንም ጠቅሷል።
ይህም ባንኩ ባለፈው ዓመት ካስመዘገበው ጠቅላላ ገቢ 148.85 በመቶ እድገት አሳይቷል ሲል ለሸገር በላከው መግለጫ ጠቅሷል።

የባንኩ ጠቅላላ ሀብት ከ15 ቢሊዮን ብር አልፏል፤ ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር 95.37 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል ተብሏል።
እንዲሁም የተቀማጭ ገንዘብ መጠን 12 ቢሊዮን ብር መድረሱም ተጠቅሷል።
በተጨማሪም ሂጅራ ባንክ በበጀት ዓመቱ 40 ሚሊዮን ዶላር አግኝቻለሁ ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር 304.5 በመቶ ጭማሪ ያሳያል ብሏል።
135 ቅርንጫፎች፣ የደንበኞችን ብዛት ደግሞ 931,148 ደርሰዋል ሲል ጠቅሷል።
ሂጅራ ባንክ የኦምኒ ፕላስ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ ተጠቃሚዎች ከ350,000 በላይ ሲሆኑ ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር 141.86 በመቶ እድገት ያሳያል ተብሏል።
ባለፉት 6 ወራት ብቻ የሀላል ፔይ ዋሌት ተጠቃሚዎች ከ811,000 በላይ ደርሰዋል የተባለ ሲሆን ያለማስያዣ የፋይናንስ አገልግሎት መጠቀም የሚያስችል ኢ-ሙራባሃ የፋይናንስ አገልግሎትን በዋሌት በማስጀመር ስኬታማ ዓመትን አሳልፌያለሁ ብሏል።
ንጋቱ ሙሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments