ሰኔ 28፣ 2016 - በኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ ያለው የመረጃ አያያዝ ብዙ ጉድለት ያለበት ነው ሲል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ተናገረ
- sheger1021fm
- Jul 5, 2024
- 1 min read
በኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ ያለው የመረጃ አያያዝ ብዙ ጉድለት ያለበት ነው ሲል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ተናገረ፡፡
መረጃን በምሰበስብበት ወቅት ተበታትኖ ነው የማገኘውም ብሏል፡፡
ኢንስቲትዩቱ እንደ ሀገር የጥናት ውጤቶችና የሆስፒታል መረጃዎች መያዝ ብዙ ስራ የሚጠይቅ ሆኖ አግኝቼዋለው ሲልም ተናግሯል፡፡
የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በጤናው ዘርፍ መረጃ እንዴት እንደሚያዝና የተያዙ መረጃዎች ለምን ለምን እንደሚጠቅሙ የተለያዩ ውይይቶች ላይ በመገኘት ተሞክሮዎችን እንደሚያካፍል ሰምተናል፡፡
ማርታ በቀለ
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Comments