top of page

ሰኔ 27 2017 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች

  • sheger1021fm
  • 5 days ago
  • 2 min read

የታንዛኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቃሲም ማጃሊዋ በመጪው የፓርላማ ምርጫ አልፎካከርም አሉ፡፡


ማጃሊዋ ቀደም ሲል በምርጫው እፎካከራለሁ ብለው እንደነበር ቢቢሲ ፅፏል፡፡


በታንዛኒያ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ለመሾም በፓርላማ አባልነት መመረጥን ይጠይቃል፡፡

ማጃሊዋ በፓርላማ አባላቱ ምርጫ የማይፎካከሩ ከሆነ ከጠቅላይ ሚኒስትርነቱ ሹመት ውጭ ይሆናሉ ተብሏል፡፡


ቃሲም ማጃሊዋ ይህን ውሳኔ ለምን እንደወሰኑ የታወቀ ነገር የለም፡፡


እሳቸውም ጉዳዩን እንዳላፍታቱት ተጠቅሷል፡፡


ይሁንና በገዢው CCM የፖለቲካ ማህበር ከፍተኛ ሹምነታቸው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡



የአሜሪካ ኮንግረስ በእጅጉ ሲያወዛግብ የቆየውን የፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕን የበጀት ረቂቅ ህግ አፀደቀላቸው፡፡


ትራምፕ ታላቅ እና ቆንጆ ሲሉ የጡሩት የበጀት ረቂቅ በህግ መወሰኛው /ሴኔትም/ ሆነ በህዝብ ተወካዮቹ ምክር ቤት በከባዱ ሲያነታርክ መሰንበቱን ቢቢሲ ፅፏል፡፡


ዲሞክራቶቹ እንደራሴዎች የበጀት ሕጉ የአሜሪካን ባለ ዝቅተኛ ገቢዎች በመጉዳት ሐብታሞቹን የሚጠቅም ነው በሚል ሲሞግቱ ሰነብተዋል፡፡


በተለይም በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ባለዝቅተኛ ገቢ አሜሪካውያንን ከጤና ማህበራዊ ዋስትና ውጭ የሚያደርግ ነው በሚል በዲሞክራቶቹ በእጅጉ ተነቅፏል፡፡


ዴሞክቶቹ በፊናቸው ሕጉን ትልቅ አስቀያሚ በሚል ቅፅ እየጠሩት ነው፡፡


ከአታካቹ ክርክር በኋላ የበጀት ህጉ በምክር ቤቶቹ መፅደቁ ታውቋል፡፡


ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዛሬ የአሜሪካ የነፃነት ቀን ከሚከበርበት እለት በተጓዳኝ ስራ ላይ እንዲውል ይፈርሙበታል ተብሏል፡፡



በአውሮፓ በእጅጉ እየጨመረ የመጣው ግለት እና የሙቀት ማዕበል በበጋው 1 ሺህ ያህል ሰዎችን ሊገድል እንደሚችል ተገመተ፡፡


እንደ ስፔን እና ብሪታንያ ባሉ አገሮች የሙቀት ማዕበሉ አሉታዊ ተፅዕኖ እየጎላ መምጣቱን አናዶሉ ፅፏል፡፡


በአውሮፓ ደቡባዊ ክፍል የሙቀት መጠኑ እስከ 46 ዲግሪ ሴሊሺየስ አሻቅቧል ተብሏል፡፡


የሙቀት ማዕበሉ በስፔን ካታሎኒያ ሁለት ሰዎችን መግደሉን መረጃው አስታውሷል፡፡


በብዙ የአውሮፓ አገሮች ሰዎች ለግለቱ እንዳይጋለጡ ማስጠንቀቂያው በላይ በላዩ ሆኗል፡፡


አሜሪካም ሆነች ጃፓን የተመሳሳይ ችግር ሰለባዎች እንደሆኑ መረጃው አስታውሷል፡፡



የአሜሪካ ኮንግረስ በእጅጉ ሲያወዛግብ የቆየውን የፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ፣ የበጀት ረቂቅ ህግ አፀደቀላቸው፡፡


ትራምፕ ታላቅ እና ቆንጆ ሲሉ የጠሩት የበጀት ረቂቅ በህግ መወሰኛው /ሴኔትም/ ሆነ በህዝብ ተወካዮቹ ምክር ቤት በከባዱ ሲያነታርክ መሰንበቱን ቢቢሲ ፅፏል፡፡


ዲሞክራቶቹ እንደራሴዎች የበጀት ህጉ የአሜሪካን ባለ ዝቅተኛ ገቢዎች በመጉዳት ሐብታሞቹን የሚጠቅም ነው በሚል ሲሞግቱ ሰንብተዋል፡፡


በተለይም በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ባለ ዝቅተኛ ገቢ አሜሪካውያንን ከጤና ማህበራዊ ዋስትና ውጭ የሚያደርግ ነው በሚል ዲሞክራቶቹ በእጅጉ ተነቅፏል፡፡


ከአታካቹ ክርክር በኋላ የበጀት ህጉ በምክር ቤቶቹ መፅደቁ ታውቋል፡፡


ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዛሬ የአሜሪካ የነፃነት ቀን ከሚከበርበት እለት በተጓዳኝ ስራ ላይ እንዲውል ይፈርሙበታል ተብሏል፡፡



ራያን ኤር የተሰኘው አየር መንገድ ትናንት የፈረንሳይ የአየር ተቆጣጣሪዎች በመቱት የስራ ማቆም አድማ ምክንያት 170 በረራዎቼን ለመሰረዝ ተገድጃሁ አለ፡፡


በዚህም የተነሳ ከ30 ሺህ በላይ የአየር መንገዱ ደንበኞች ጉዞ እንደተስተጓጎለ ቢቢሲ ፅፏል፡፡


የፈረንሳይ የአየር ተቆጣጣሪ ሰራተኞች ህብረቶች ከትናንት አንስቶ በ2 ቀናት የስራ ማቆም አድማ ላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡


አድማው በፈረንሳይ ሩብ ያህሉን በረራዎች ማስተጓጎሉ ተጠቅሷል፡፡


የአየር ተቆጣጣሪ ሰራተኞቹ ወደ አድማ የገቡት የተሻለ የስራ ሁኔታ አንዲፈጠርላቸው በመጠየቅ ነው ተብሏል፡፡


የአገሪቱ የትራንስፖርት ሚኒስትር የአድመኞቹ ጥያቄም ሆነ እርምጃቸው በጭራሽ ተቀባይነት የለውም ማለታቸው ተሰምቷል፡፡


ጊዜው በፈረንሳይም ሆነ በሌሎች የአውሮፓ አገሮች የአየር ተጓጓዦች ብዛት በጣሙን የሚጨምበት እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡


የኔነህ ከበደ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…





Commentaires


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page