ሰኔ 27 2017 - ሱዌይስ ሞተርስ፤ የነዳጅና የኤሌክትሪክ ስርዓትን አጣምረው የያዙ ሃይብሪድ መኪኖችን በሃገር ውስጥ መገጣጠም መጀመሩን ተናገረ
- sheger1021fm
- 5 days ago
- 1 min read
ላለፉት 7 ዓመታት በአውቶሞቲቭ ዘርፍ ተሰማርቶ ባለሁለት እግር ተሸከርካሪዎችን ለገበያ ሲያቀርብ የነበረው ሱዌይስ ሞተርስ ካለፈው ዓመት ጀምሮ በተለይ የጅቱር ብራንድ ሆኑ የነዳጅና የኤሌክትሪክ ስርዓትን ያጣመሩ ሃይብሪድ ተሸከርካሪዎችን በጅግጅጋ ከተማ ባለው ፋብሪካው እየገጣጠመ ለገበያ እንደሚያቀርብ የነገሩን የድርጅቱ የሽያጭ ባለሞያ አቶ መሃመድ አብዱል ቃድር ናቸው፡፡
በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ወደ ሃገር ውስጥ ማስገባት ከተከለከለ ወዲህ ድርጅቱ ተሰማርቶበት ከነበረው ሞተርና ባጃጆችን ለገበያ ከማቅረብ ፊቱን የተለያዩ አይነት ብራንድ ያላቸውን ተሸከርካሪዎች በሃገር ውስጥ ወደ መገጣጠም ማዞሩንም ነግረውናል፡፡

ሃይብሪድ ተሸከርካሪዎቹ በተጠቃሚዎች ዘንድ ተመራጭ ናቸው የሚሉት አቶ መሃመድ ተሸከርካሪዎቹን ከ4.5 ሚሊዮን ብር ጀምሮ ዋጋ እንዳላቸውና ለግዢ የሚሆን ብድር ለማመቻቸት ከባንኮች ጋር እየተነጋገሩ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
ሱዌይስ ሞተርስ ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በአዳማ፣ደብረዘይት፣ሻሸመኔ፣ሃዋሳ፣መቀሌና ባህርዳር የመሸጫ ቦታዎች ያሉት ሲሆን ከ2 ዓመት በኋላ በአዲስ አበባ ተጨማሪ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ አንደሚገነባ ተናግሯል፡፡
በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ የሚገጣጥማቸውን ጨምሮ ከ1,000 በላይ ተሸከርካሪዎችን ለኢትዮጵያ ገበያ አቅርቤያለሁም ብሏል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…… https://www.mixcloud.com/ShegerFM/6575/
ምታምር ፀጋው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Commentaires