top of page

ሰኔ 27፣ 2016 - ‘’የሰብአዊ መብት የሚባል አዋጅ፣ ተቋማት እና አሰራርን፤ መፈተሸ የስፈልጋል’’ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

  • sheger1021fm
  • Jul 4, 2024
  • 1 min read

‘’የሰብአዊ መብት የሚባል አዋጅ፣ ተቋማት እና አሰራርን፤ መፈተሸ የስፈልጋል’’ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ፡፡


ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአንድ የፓርላማ አባል በሀገሪቱ የሰብአዊ መብት ጥሰት፣ የጅምላ ግድያዎች እስራቶች በመንግስት ሀይሎች እየተፈጸመ ነዉ የሚል ጥያቄ በቀረበላቸዉ ወቅት ነው ይህንን የተናገሩት፡፡


የሰብአዊ መብት በግርድፉ ሲታይ ‘’ደስ የሚል ቋንቀ ነዉ’’ ያሉት ዐቢይ አህመድ ‘’የሰብአዊ መብት የሚባል አዋጅ፣ ተቋማት እና አሰራርን መፈተሸ የስፈልጋል እኛ ደመወዝ የማንከፍለዉ፣ ሌሎች ሃይሎች የቀጠሩት፣ ለሌሎች ሪፖርት የሚያደርግ ተቋም ኢትዮጵያ ዉስጥ ከፈቀድን ምን ሊፈጠር እንደሚችል ለእናንተ መተዉ ነዉ’’ ሲሉ ለእንደራሴዎቹ ነግረዋል፡፡


‘’በየትም ቦታ ያሉ እኔ የማያቸዉ የሰብአዊ መብት ተቋማት ልክ እንደ መርፌ የራሳቸዉን ቀዳዳ መስፋት የማይችሉ እና የራሳቸዉን ድክመት ማየት የማይችሉ ናቸዉ’’ ብለዋል፡፡


‘’ይሄ ጥሩ አይደለም ሀገር ያፈርሳል ተቋሞቻችን ፅዱ ማድረግ አለብን፤ እነዚህ ተቋማት ከሁለት ተጽእኖ ነጻ መዉጣት አለባቸዉ’’ ብለዋል፡፡


‘’ከኢትጵያ መንግስት ተጽኖ ነጻ መሆን አለባቸዉ፤ ከሌላም ሀገራት ተጽእኖዎች ነጻ መሆን አለባቸዉ፤ አሁን ያሉት ከኛ ነጻ ሆኑና እንደዚያ አይሰራም’’ ሲሉ ተናግረዋል፡፡


ያሬድ እንዳሻው


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page