top of page

ሰኔ 27፣ 2016 - ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን ባህላዊ የህክምና ስራን የተመለከቱ ማስታወቂያዎች በርክተዋል

  • sheger1021fm
  • Jul 4, 2024
  • 1 min read

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን ባህላዊ የህክምና ስራን የተመለከቱ ማስታወቂያዎች በርክተዋል፡፡


አብዛኛዎቹም ከህክምና ስራው ውጪ የሆኑና ማጭበርበሪያ የታከለባቸው በመሆኑ ብዙዎችን ገንዘባቸው እያስነጠቀ መሆኑ ተነግሯል፡፡


የአዲስ አበባ #የባህል ህክምና አዋቂዎች ማህበር በበኩሉ አባል የሆኑትን እየተቆጣጠርኩ ነው ብሏል፡፡


ነገር ግን ይህ ህገ- ወጥ ስራ የባህላዊ ህክምና ስራውን ስም እያጎደፈብን ነው ብሏል፡፡

ባህላዊ የህክምና ጥበቡ ቀድሞ የሚታወቅበት የተለያዩ መፈወሻዎች ቢኖሩም በየማህበራዊ መገናኛ ብዙኃን የሚተላለፉ አሳሳች ማስታወቂያዎች በርክተዋል፡፡


ለግርማ ሞገስ፣ ለስልጣን፣ በውጭ ሀገር መኖሪያ ፈቃድ ላላገኙ፣ ገንዘብ ለሚያባክኑ የሚሉና ሌሎችም ይጠቀሳሉ፡፡


ይህም በህጋዊነት ፈቃድ አውጥተው የሚሰሩትን ባለሙያዎች የሚጎዳ ዘርፉንም ስም የሚያጎድፍ መሆኑን የነገሩን የአዲስ አበባ የባህል ህክምና አዋቂዎች ማህበር ፕሬዝዳንቱ መሪጌታ መንግስቱ ናቸው፡፡


ማስታወቂያዎቹን በመመልከት ያለምንም ማረጋገጫ በአጭበርባሪዎች ገንዘባቸውን የሚቀሙ ሰዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉም መክረዋል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ…


ምህረት ስዩም


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page