‘’ኢትዮጵያ ውስጥ መፈንቅለ መንግስት እናካሄለን ያሉ ሰዎች በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ውይይት አካሂደው እንደነበር’’ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ፡፡
‘’የመፈንቅለ መንግስት ለማድረግ ውይይት የተካሄደው በቅርቡ ነው’’ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀሳቡን ባለቤቶች ''አንዳንድ አባቶቻችን (ታላላቆቻችን)'' ሲሉ ገልፀዋቸዋል፡፡
‘’መፈንቅለ መንግስት ኢትዮጵያ ውስጥ አይሳካም፣ እኛ ወታደሮች ነን መፈንቅለ መንግስት እንዳይሳካ አድርገን ነው ተቋማት የሰራነው’’ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተደምጠዋል፡፡
‘’ኢትዮጵያ ውስጥ መፈንቅለ መንግስት አንዴ ተሳካ የዛሬ 50 ዓመት’’ ያሉት ዐቢይ አህመድ ‘’ከ50 ዓመት በኋላ ብዙ የሚረቡ እና የማይረቡ ሙከራዎች ነበሩ ግን አልተሳኩም’’ ሲሉ ጠቅሰዋል፡፡
‘’አሁንም ጭራሽ አይሳካም’’ ሲሉም አክለዋል፡፡
‘’የመፈንቅለ መንግስት እናካዳለን ብለው ውይይት ያደረጉትን’’ እና ‘’ወንድሞቼ እና ታላላቆቼ’’ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጠቀሷቸው አካላት ‘’ጊዜ አታባክኑ፣ የወዳጆቻችንንም ሀገር ገንዘብ አታባክኑ፣ ገስት ሀውስም አታጣቡ ፣ አይሳካም’’ ሲሉ ምክር ሰጥተዋል፡፡
‘’ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን መፈንቅለ መንግስት አይሳካም እንጂ፤ ቢሳካ ኢትዮጵያን ሌላ ሱዳን እናደርጋት ይሆናል እንጂ ሀገር ሆና እኛም መንግስት ሆነን አንቀጥልም’’ ብለዋል፡፡
ንጋቱ ሙሉ
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Comments