top of page

ሰኔ 27፣ 2016 - በዞኑ በተከሰተው ድርቅ የመኖ እጥረት በመግጠሙ 14,900 የሚሆኑ እንስሳት ሞተዋል

በመኖ እጥረት ምክንያት ይህን ያህል እንስሳት ሞተዋል፤ ይህን ያህሉ ደግሞ በከፍተኛ ደረጃ ተጎድተዋል የሚሉ መረጃዎች በተለያዩ ጊዜያት ይደመጣሉ፡፡


የግብርና ሚንስቴር በበኩሉ ‘’ሀገሪቱ ውስጥ የእንስሳት መኖ እጥረት ሳይሆን የዋጋ መወደድ ነው’’ ያጋጠመው የሚል ምላሽ ሲሰጥ ይታያል፡፡


ሰሞኑን በዋግህምራ ዞን ውስጥ በተከሰተ ድርቅ ምክንያት የእንስሳት ሞት መመዝገቡን ሰምተናል፡፡


በዞኑ በተከሰተው ድርቅ የመኖ እጥረት በመግጠሙ 14,900 የሚሆኑ እንስሳት ሞተዋል ሲሉ የዋግህምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ተናግሯል፡፡


አሁንም የእንስሳት መኖው በክረምቱ ወቅት ካልተገኘ የሚሞቱ የእንስሳት ቁጥር ከዚህ ከፍ ሊል እንደሚችል የፅህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ምህረት መላኩ አሳስበዋል፡፡



Comentários


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page