top of page

ሰኔ 26፣ 2016 - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ፖላንድ ዋርሶ የበረራ መስመር መክፈቱ ተሰማ

  • sheger1021fm
  • Jul 3, 2024
  • 1 min read

ይህ በረራ አየር መንገዱ በአውሮፓ የሚደረገውን መዳረሻ ወደ 24 ከፍ ያደርገዋል ተብሏል።


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ይህ በረራ መከፈቱ የሁለቱን ሀገሮች ወዳጅነት ከፍ ያደርገዋል ብለዋል።


በማዕከላዊ አውሮፓ ወደ ምትገኘው ፖላንድ ዋርሶ ከተማ የተከፈተው አዲስ በረራ ንግድ እንዲቀላጠፍ ቢዝነስና ስራም እንዲፍታታ ያግዛል ተብሏል።


ከኢትዮዽያም በተጨማሪ በፖላንድና በተቀረው አፍሪካ ያለው ቢዝነስና ቱሪዝም እንዲበረታ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱም ከፍ እንዲል የበረራ መስመሩ እንደሚበጅ ተሰምቷል፡፡


የኢትዮዽያ አየር መንገድ በብሔራዊ ደረጃ ከናይጄሪያ መንግስት ጋር ሊያቋቁመው የነበረው አየር መንገድ መገታቱ ተሰማ፡፡

የኢትዮዽያ አየር መንገድ ይህንኑ ስራ ለማቀላጠፍ በስራና እንቅስቃሴ ላይ የነበረ ቢሆንም ጉዳዩ ለግዜው መገታቱን ሰምተናል።


በብሔራዊ ደረጃ እንዲቋቋም የተፈለገው አየር መንገድ ለግዜው የተገታው በ ናይጄሪያ መንግስት ነው ተብሏል።


የናይጄሪያ መንግስት ጉዳዩ እንዲዘገይ የፈለገው በግዜ ሂደት ማጥናት እፈልጋለሁ ብሎ መሆኑን የኢትዮዽያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ነግረውናል።


በተመሳሳይ የስዋቲኒ መንግስት መንግስት ከኢትዮዽያ አየር መንገድ ጋር የአብረን እንስራ ጥያቄ ማቅረቡን ሰምተናል።


በዚሁ ጉዳይ ላይም የኢትዮዽያ አየር መንገድ ጊዜ ወስዶ እያጠናው መሆኑ ተነግሯል።


ተህቦ ንጉሴ


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page