top of page

ሰኔ 26፣ 2016 - የሀይማኖት አባቶች የእርስ በእርስ ግድያና መጠፋፋት እንዲቆም የድርሻቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ

የሀማኖት አባቶችና አስተማሪዎች በኢትዮጵያ ያለውን የእርስ በርስ ግድያና መጠፋፋት እንዲቆም የሃይማኖት አባቶች ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸው የተናገሩት የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ብናልፍ አንዱአለም ናቸው፡፡

 

የሰላም ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት የሃይማኖት ተቋማቶቻችን ለዘላቂ ሰላማችን በሚል መሪ ቃል ከሁሉም ቤተ እምነቶች ከተወጣጡ የሃይማኖት መሪዎችና አስተማሪዎች ጋር እየተከናወነ ባለው ኮንፍረስ ላይ ነው፡፡

 

የሰላም ሚኒስትሩ የጋራ የሆነችውን ኢትዮጵያ ካለችበት አለመረጋጋት ወጥታ ሰዎች በሰላም የሚኖሩባት አገር እንድትሆን የአይማኖት አባቶች ድርሻቸው ከፍተኛ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

 

ከቂምና ከበቀል ነፃ የሆነ ትውልድ ለመፍጠር የሃይማኖት መምህራን የማይተካ ድርሻ እንዳላቸው ሚኒስትሩ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር አስረድተዋል፡፡

ሰላም በአገር ደረጃ ያስፈልገናል ያሉት የሰላም ሚኒስትሩ አሁን ግን በአገሪቱ ሰላም በመጥፋቱ እዚህም እዚያም የሚታዩ ግጭቶች እና አለመረጋጋቶች ወንድም ወንድሙን እንዲገድል አድርገዋል ብለዋል፡፡

 

በአገሪቱ ያለው አለመረጋጋት ነጋዴው እንዳይነግድ፣ አርሶ አደሩ እንዳያርስ፣ ተማሪው እንዳይማር ማድረጉን ብናልፍ አንዱአለም ተናግረዋል፡፡

 

በተለያዩ አካባቢዎች የተፈጠሩ ግጭቶችና አለመረጋጋቶች ሰላማዊ ሰዎች እንዳይንቀሳቀሱ ከማድረጉም በላይ ሀገር ብዙ አንድታጣ  አድርጓታል ብለዋል፡፡

 

ከእርስ በእርስ መጠፋፋትና መገዳደል እንዴት መውጣት እንዳለብን ብለው የሃይማኖት አባቶች ሊጠቁሙ ይገባል ብለዋል፡፡

 

ኢትዮጵያ ሁሉም በሰላምና ተከብሮ የሚኖሩባት አገር እንድትሆን፤ የሃይማኖት መሪዎች ሃይማኖታዊ ተልዕኳቸውን እንዲፈፅሙ ሚኒስትሩ ጠይቀዋል፡፡

 

ኢትዮጵያ ፍትህ የሰፈነባት እና ሁሉም በሰላም የሚንቀሳቀሱባት አገር እንድትሆን ከ98 በመቶ የሚሆነውን የአገሪቱ አማኝ የሆኑባት አገር የሚያስተምሩ የሃይማኖት አባትና የሃይማኖት መሪዎች መከባበር እንዲኖር ማስተማር ከእናንተ ይጠበቅባቸዋል ሲል የሃይማኖት አባቶቹን ሚኒስትሩ ጠይቀዋል፡፡

 

 

Comments


bottom of page