የአፍሪካ ሀገሮች ብድር በጠቅላላው 2 ትሪሊየን ዶላር መድረሱ ተሰምቷል።
ይህም ሀገሮቹ አጠቃላይ ካላቸው ሀብት ወይም ብሔራዊ ምርት 65 በመቶ ነው።
ይህ ብድር በጠቅላላው ብሔራዊ ምርት 50 በመቶ መብለጥ እንደሌለበት ጥናት ተናግሯል።
የብዙዎቹ ሀገሮች ብድር ከመክፈል አቅማቸው በላይ ነው ።
ለአፍሪካ ልማት ባንክ በቀረበው ጥናት መሰረት አብዛኛዎቹና ትልቅ ተበዳሪዎች ሀገሮች ከ4 አይበልጡም።
ትልቋ ተበዳሪ ሀገር ደቡብ አፍሪካ ስትሆን 288 ቢሊየን ዶላር ተበድራለች
ናይጄሪያ 181 ቢሊየን ዶላር፣ አልጄሪያ 102 ቢሊየን ዶላር፣ ሞሮኮ 92 ቢሊየን ዶላር የተበደሩ ናቸው።
እነዚህ ሀገሮች የአፍሪካን ብድር 60 በመቶ ወስደዋል።
የተቀሩት የአፍሪካ ሀገሮች 745 ቢሊየን ዶላር ብድር ወስደዋል።
ተህቦ ንጉሴ
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Comments