ሰኔ 26፣ 2016 - ህዝብን ለመጥቀም ተመዝግበው የግል ጥቅማቸው የሚያሳድዱ ድርጅቶችን በብርቱ እየተቆጣጠርኩ ነው ሲል ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ለሸገር ተናግሯል
- sheger1021fm
- Jul 3, 2024
- 1 min read
በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅትነት ተመዝግበው በአግባቡ ስራቸውን በማይከውኑት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ ጀምሬአለሁ ሲል የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ተናገረ፡፡
ምዝገባ ካደረጉ በኋላ ምንም ስራ ሳይጀምሩ እስከ 2 ዓመት የሚቆዩ አሉም ተብሏል፡፡
ስራ ጀምረውም ብዙ ሳይጓዙ የሚዘጉ ድርጅቶችም በርካቶች መሆናቸው ተነግሯል፡፡

በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅትነት ከተመዘገቡ በኋላ ስፈልጋቸው ያሉበት ራሱ ማወቅ የሚቸግረኝ አሉ ብሏል ባለስልጣኑ፡፡
ይህ አይነት ችግር የሚበረታው፤ በተለይም ሀገር በቀል በሆኑት ድርጅቶች ላይ ነውም ተብሏል፡፡
ሀገርን እና ህዝብ ለመጥቀም ተመዝግበው ግን የግል ጥቅማቸው የሚያሳድዱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችንም በብርቱ እየተቆጣጠርኩ ነው ሲል የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ለሸገር ተናግሯል፡፡
በባለስልጣኑ የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ሃላፊ በፍቃዱ ወልደሰንበት ለሀገር በቀሎቹ ክትትል እንዲሁም ድጋፍ በባለስልጣኑ እንደሚደረግላቸው ያስረዳሉ፡፡
በኢትዮጵያ ተመዝገበው፤ በተለያዩ ጊዜያት የሚዘጉት የሲቪል ማህረሰብ ድርጅቶች ጥቂት የሚባሉ አይደሉም፡፡
አቶ በፍቃዱ እንደሚያስረዱት ከሆነ፤ ከእነዚህ መካከል የሚበዙት የሚዘጉት በሚገጥማቸው የገንዘብ እጥረት ምክንያት ነው፡፡
በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከ5000 በላይ የተመዘገቡ ሀገርበቀል እና የውጭ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አሉ ተብሏል
ማያዘዋል ጌታሁን
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Comments