top of page

ሰኔ 26፣ 2016 - ሀገርን ከፍተኛ አደጋ ላይ የሚጥለውን የኬሚካል ክምችት ለማስወገድ ምን እየተሰራ ይሆን?

በህንጻ ግንባታ ላይ የደህንነት መከላከያ ባላሟሉ አስገንቢዎች ላይ እስከ እስራት የሚያደርስ ህግ መዘጋጀቱ ተሰማ።


አዲሱ ህግ ስራ ላይ ሲውል በህንጻ ግንባታ ላይ የሚስተዋሉ የደህንነት ችግሮች እና ስጋቶችን ይቀርፋልም ተብሎለታል።


በህንጻ ግንባታ ላይ በሚስተዋሉ የጥንቃቄ ጉድለት፤ ከጊዜ ወደ ጊዜ የሰዎች ሞት እና የአካል ጉዳት እየጨመረ መምጣቱ አዲሱ ህግ እንዲወጣ ምክንያት ሆኗልም ተብሏል።


በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የኮንስትራክሽንና መሰረተ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ መዲና አህመድ፤ ህንፃዎች በሚገነቡበት ሰዓት በአካባቢው እና በህብረተሰቡ ላይ ስጋት በሆነ መልኩ በሚገነቡና ለሰራተኞቻቸው ጭምር የደህንነት መከላከያ ግብአቶች ሳያሟሉ በተገኙ አስገንቢዎች ላይ ከፈቃድ መቀማት እስከ እስራት ድረስ እንዲቀጡ በህጉ ተቀምጧል ሲሉ ነግረውናል።


ከዚህ ባለፈም የስራ ተቋራጮች የብቃት ማረጋገጫ ከሌላቸው ወደ ስራ እንዳይገቡም ህጉ ይከለክላል ብለዋል።


አዲሱ ህግ በሰራተኞች እና በአካባቢው ባሉ ማህበረሰቦች ላይ በጥንቃቄ ጉድለት ምክንያት ጉዳት እንዳይደርስ የቅድመ መከላከል ስራ እንዲሰራ እና ጥንቃቄ እንዲደረግ በማሰብ እንጂ በህንፃ አስገንቢዎች ላይ ጫና ለማሳደር አይደለም ሲሉ ወ/ሮ መዲና ተናግረዋል።


ህጉ መቼ እንደሚፀድቅ እና የእስር ቅጣቱ እስከ ምን ያህል ጊዜ የሚለውን በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ተደርጎበት ሲፀድቅ ይፋ እንደሚደረግም ስራ አስፈፃሚዋ ተናግረዋል።


ፍቅሩ አምባቸው


Comments


bottom of page