top of page

ሰኔ 25፣ 2016 - ኢትዮጵያና ሶማሊያ በቱርክ አሸማጋይነት የጀመሩትን ንግግር ለሁለተኛ ዙር ለመቀጠል ተስማሙ

  • sheger1021fm
  • Jul 2, 2024
  • 1 min read

ኢትዮጵያና ሶማሊያ በቱርክ አሸማጋይነት የጀመሩትን ንግግር ለሁለተኛ ዙር ለመቀጠል ተስማሙ፡፡


በሁለቱ ሃገራት መካከል የተፈጠረውን ዲፕሎማሲያዊ ውጥረት ለማርገብ በቱርክ አንካራ ትናንት የተጀመረው የመጀመሪያ ዙር ንግግር ከፍተኛ የቱርክ ዲፕሎማቶች በተገኙበት መካሄዱ ተሰምቷል፡፡


የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳን ከሁለቱ ሃገራት ንግግር በኋላ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡


የመካከለኛውን ምስራቅ ጉዳይን በመዘገብ የሚታወቀው አል ሞኒተር የቱረክን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጠቅሶ እንደዘገበው በመጀመሪያው ዙር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ እና የሶማሊያ አቻቸው አህመድ ፊቅ የመሩት የሁለቱ ሃገራት ልዑክ የቱርክ ዲፕሎማቶች ባሉበት የመጀመሪያው ዙር ንግግር አድርገዋል፡፡


ሁለተኛ ዙር ንግግራቸውንም በመጭው መስከረም ወር መጀመሪያ በቱርክ አሸማጋይነት ለመቀጠል ተስማምተዋል ተብሏል፡፡


ከሶማሊያ የግዛቴ አካል ነች ከምትላት ሶማሌላንድ ጋር ኢትዮጵያ በወደብ ጉዳይ የመግባቢያ ስምምነት ከፈረመች ወዲህ ሁለቱ ሃገራት የገቡበትን ዲፕሎማሲያዊ ውጥረት በንግግር ለመፍታት ትናንት ያደረጉት ንግግርም ተስፋ ሰጭ ነው ብለውታል የቱርኩ የው ጉዳይ ሚኒስትር፡፡


የቀጠናውን መረጋጋት በሚያረጋግጥ መልኩ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ችግሩን በሰላም ለመፍታት የጀመሩት ንግግር በመጭው መስከረም ለሁለተኛ ዙር እንደሚቀጥሉም ስምምነት ላይ ተደርሷል ብለዋል የቱርኩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፡፡


ቱርክ የሶማሊያን የግዛት አንድነት እንደምትደግፍ ጠቅሳ ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር ያደረገችው የመግባቢያ ስምንት መንቀፍ የሚታወስ ነው፡፡


በሶማሊያም ወታደራዊ ካምፕ ገንብታለች፡፡


በሌላ በኩልም ከኢትዮጵያ ጋር ጥሩ የወዳጅነት ግንኙነት ያላት ሲሆን ከ3 አመት በፊት በርካታ ድሮን ለኢትዮጵያ መሸጧን ዘገባው አስታውሷል፡፡


ትዕግስት ዘሪሁን


Comentários


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page