በድንበር አካባቢ የሚነሱ የእንስሳት በሽታዎችን ለመከላከል ከሱዳን በስተቀር ከሁሉም ጎረቤት ሀገራት ጋር እየተሰራ ነው ተባለ፡፡
ይህንን ያለው የግብርና ሚኒስቴር ነው፡፡
ግብርና ሚንስቴር ድንበር አካባቢ የሚነሱ የእንስሳት በሽታዎችን ለመከላከል የሚያስችለውን ስምምነቱ ከሁሉም ጎረቤት ሀገራት ጋር ተፈራርሞ እየሰራ መሆኑን ሰምተናል፡፡
የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሳ እንደነገሩን ከሱዳን ጋር ተመሳሳይ ስምምነት ተደርሶ የነበረ ቢሆንም ስምምነቱ እንደተደረሰ በኢትዮጵያ እና በሱዳን ውስጥ የነበሩ ጦርነቶች ወደ ትግበራ እንዳይገባ ችግር ሆኗል ብለዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም ኢትዮጵያ በ2027 እንደ ‘’ደስታ’’ ያሉ የእንስሳት በሽታዎች ለማጥፋት አቅዳለች ያሉት ሚንስትር ዴኤታው ለዚህም ከጎረቤት ሀገራት ጋር በትብብር እየተሰራ ነው ይላሉ፡፡
ለዚህ ስራ የብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት የተለያዩ ክትባቶችን እያመረተ በስፋት እያቀረበ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት የክትባት ምርትና የመድሀኒት ምርት ዳይሬክተር ወ/ሮ ብርሀን ደመቀ በበኩላቸው ኢንስቲትዩቱ ከሀገር ውስጥ በተጨማሪ ከ22 ለሚበልጡ የአፍሪካ ሀገራት ክትባቶችን እያቀረበ ነው፡፡
ከክትባት ውጪ የሚያመርታቸው የእንስሳት መድሃኒቶች በስፋት እያመረተ ሌሎች ሀገራት እያቀረበ አይደለም ያሉ ሲሆን ይህንን ችግር በመቅረፍ ክትባቶችና መድሃኒቶች በተሻለ ጥራት ለአካባቢው ሀገራት ለማቅረብ ውጥን አለው፡፡
ከጎረቤት ሀገራት የሚነሱ ወረርሽኖች ለመከላከልና ክትባቶች በጋራ ለመስጠት ጥሩ ቅርርብ አለ ተብሏል፡፡
ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት ሀገሪቱ ከውጪ የምታስገባቸው መድሃኒቶችና ክትባቶች ሙሉ ለሙሉ በሀገር ውስጥ ለመተካትና በስፋት አምርቶ ለውጪ ገበያ ለማቅረብ ወደፊት ያቀደው ስራ መሆኑን ሰምተናል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ… https://tinyurl.com/5n7paxr6
ተያያዥ ዘገባን ለማንበብ…
በረከት አካሉ
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Comments