ሰኔ 24 2017 -''ጨረታ ወጥቶላቸው የግንባታ ስራቸው የተጀመሩ መንገዶችን ብቻ ለመጨረስ 500 እስከ 600 ቢሊየን ብር ያስፈልጋል ''
- sheger1021fm
- Jul 1
- 1 min read
ከዚህ ቀደም የተጀመሩ የመንገድ ፕሮጀክቶች ቢኖሩም በወቅቱ ባለመጠናቀቃቸው ልዩ ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል ተባለ፡፡
መንግስት ለመንገድ ፕሮጀክቶች የሚደለድለው በጀት ይበል የሚያሰኝ ቢሆንም አንዳንድ አካባቢዎች ላይ የተጀመሩ ፕሮጀክቶች የበለጠ ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ ተነስቷል፡፡
ይህ ጥያቄ የተነሳው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ2018 ረቂቅ በጀት ላይ በሚያደርገው ውይይት ላይ ነው፡፡
ሁለት ክልሎችን ያገናኛል የተባለው የነቀምት ቡሬ መንገድ ግንባታ እስካሁን ያልተጠናቀቀ መሆኑን ያነሱት የምክር ቤት አባሉ አቶ ብዙአየሁ ደገፋ ሌላኛው ጋምቤላን እና ደንቢዶሎን የሚያገናኘው የመንገድ ግንባታም ስራው አለመጀመሩን አንስተዋል፡፡

በሌላ በኩል እቅድ የተያዘላቸው የመንገድ ፕሮጀክቶች በ2018 በጀት ዓመት ውስጥ ያልተካተቱ መኖራቸውን ያነሱት የምክር ቤት አባሉ ለእነሱ ወደፊት ምን እንደታሰበ ጠይቀዋል፡፡
የ2018 ረቂቅ በጀት ላይ ከምክር ቤት አባላቱ ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ የምክር ቤቱ አባላት የተነሱት ጥያቄዎች ተገቢ ናቸው ብለዋል፡፡
ምክር ቤቱ ያፀደቃቸውን የመንገድ ፕሮጀክቶች ለመጨረስ 1.5 ትሪሊየን ብር ያስፈልጋል ያሉት ሚኒስትሩ ጨረታ ወጥቶላቸው የግንባታ ስራቸው የተጀመሩ መንገዶችን ብቻ ለመጨረስ 500 እስከ 600 ቢሊየን ብር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ፋሲካ ሙሉወርቅ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Commenti