ሰኔ 24 2017 - ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የደንበኞቼ ቁጥር 10 ሚሊዮን ደርሷል አለ
- sheger1021fm
- Jul 1
- 1 min read
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የደንበኞቼ ቁጥር 10 ሚሊዮን ደርሷል፣ ይህም ከፍተኛ ስኬት ነው አለ፡፡
ኩባንያው የኢትዮ ቴሌኮም ማማዎች ላይ ለሚያስቀምጠው ኔትወርክ ማሰራጫ በየወሩ 3 ሚሊዮን ዶላር እየከፈለ መሆኑንም ሰምተናል፡፡
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት ግማሹን የሀገሪቱን ህዘብ ማስጠቀም የሚያስችል ኔትወርክ መዘርጋቱን ዛሬ በሰጠው መግለጫ ተናግሯል፡፡
አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን ፍቃድ ከወሰደ አራት ዓመት አንደሞላው ያስታወሰው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ፤ ቢዚህ ጊዜም ከ300 ቢሊዮን ብር በላይ ኢንቨስት አንዳደርገ ዋና ስራ አስፈጻሚው ዊም ቫንሄለቱት አስረድተዋል፡፡
ኩባያው ከ150 በላይ በሆኑ ከተሞች 3,141 የኔትወርክ ማማዎችን ገንብቻለሁ ብሏል።
በዚህም 10 ሚሊዮን ንቁ ደንበኞች ማፍራቱን፣ 7.1 ሚሊዮን የሞባይል ዳታ አገልግሎት ተጠቃሚዎች እንዳሉትም ዋና ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል። በየቀኑም 31000 አዳዲስ ደንበኞችን እያገኘሁ ነው ብሏል፡፡

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አሁንም በኢንቨስትመንት ደረጃ ላይ መሆኑን ተናግሮ በዚህ በጀት ዓመት ለሥራ ማስኬጃ ያወጣው ወጪ ካስገባው 2.7 ቢሊዮን ገቢ በ47 ቢሊዮን ብር የሚበልጥ ነው ብሏል።
ኩብንያው የ4 ዓመት ጉዞው ከፍተኛ ስኬት የተመዘገበበት መሆንን ስራ አስፈጻሚው ዊም ቫንሄለቱት አስረድተዋል፡፡
በኢትዮጵያ ያለው የቴሌኮም ዘርፍ የሚያስከፍለው የሞባይል ዳታ ክፍያ ርካሽ የሆነና መስተካከል አንዳለበትም ስራ አስፈጻሚው ጠይቀዋል፡፡
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በመጪዎቹ 3 ዓመታት አስካሁን ኢንቨስት ያደረገውን በእጥፍ በማሳደግ የኔትውርክ ማማዎቹን ብዛት ከ6,000 በላይ፣ ከሀገሪቱ ህዝብ ደገሞ 80 በመቶውን ለመድረስ ማሰቡን ተናግሯል፡፡
ኩባንያው 900 ሠራተኞች አንዳሉት ከአነዚህ ውስጥ 97 በመቶ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን መሆናቸውንም አስረድቷል።
ንጋቱ ሙሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments