top of page

ሰኔ 24፣ 2016 - የወልቃይት፣ ጠለምት እና የራያ ማህበረሰቦች ላነሷቸው የማንነትና የማካለል ጥያቄ በጸጥታ ምክንያት መልስ መስጠት አልተቻለም ተባለ

ይህ የተባለው በፌድሬሽን ምክር ቤት የማንነት የአስተዳደር ወሰን እና የሰላም ግንባታ ቋሚ ኮሚቴ የ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱን ለፌድሬሽን ምክር ቤት ባቀረበበት ወቅት ነው፡፡


ከማንነት ይታወቅልኝ እና መካለል ጋር በተያያዘ የወልቃይት የራያ እና የጠለምት ማህበረሰቦች ያነሷቸውን ጥያቄዎች በተመለከተ ለውሳኔ ሂደት የሚያስፈልጉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ ቢሆኑም በቦታው ተገኝተው ተጨማሪ መረጃዎችን ለመሰብሰብ በአካባቢው በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት እንዳልተቻለ ቋሚ ኮሚቴው በሪፖርቱ ተናግሯል፡፡


በዚህም በአካባቢው የሰላም ሁኔታ ሲሻሻል ጉዳዩ በቀጣይ ትኩረት ተሠጥቶት የሚሰራው ይሆኗል ሲል የፌድሬሽን ምክር ቤት የማንነት የአስተዳደር ወሰን እና የሰላም ግንባታ ቋሚ ኮሚቴ ሲናገር ሰምተናል፡


ያሬድ እንዳሻው


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page