በአዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከተሞች የነበሩት ሰበታ፣ ቡራዩ፣ ለገጣፎ ለገዳዲ፣ ሱሉልታ፣ ገላንና መናገሻ፤እንዲሁም 40 የገጠር ቀበሌዎች ባለፈው ዓመት ጥር ወር “የሸገር ከተማ አስተዳደር’’ በሚል በአንድ መደራጀታቸው ይታወሳል።
የከተማ አስተዳደሩ በስሩ 12 ክፍለ ከተሞች እና 36 ወረዳዎችን ይዞ ነው የተደራጀው።
የሸገር ከተማ አስተዳደርን በአዲስ መልክ ማደራጀት ያስፈለገው በዋናነት ለነዋሪዎቹ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት እንደሆነ ተጠቅሷል።
ለዚህም ሲባል ከተማዋን ‘’ስማርት እና ዲጂታል’’ የማድረግ ስራ ይሰራል ተብሏል።
ለመሆኑ የከተማ አስተዳደሩ በአዲስ መልክ ከተደራጀ በኋላ ባሉት አንድ ዓመት ከስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ምን ተሰርቷል?
እውን እንደተባለው ዲጂታል እና ስማርት ከተማ እየሆነች ነው ወይ ስንል ጠይቀናል?
ንጋቱ ረጋሳ
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Comentários