ኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ4 ቢሊየን ዶላር በላይ እያወጣች ነዳጅ ወደ ሀገር ውስጥ ታስገባለች፡፡
ነገር ግን በየጊዜው በመሀል ሀገር ስራና ቢዝነስ ባለበት ከተማ ነዳጅ ይጠፋል።
ግዜ እየጠበቀ በየማደያ ቸርቻሪዎች ጋር የሚታየው እረጃጅም ሰልፍና መንፏቀቅ ከየት የመጣ ነው?
ነዳጅ ገብቷል፤ ተገዝቷል ከተባለስ ለምን ሰልፍና የማደያ ላይ ትርምስ ጠባይ እየሆነ መጣ?
በዓመት ቢያንስ ከሶስት ግዜ በላይ ይህ ነገር በየማደያ አዳዮች ይታያል፡፡
በዚህ ጉዳይ የጠየቅናቸው የኢትዮዽያ ነዳጅ አዳዮች ማህበር ዋና ፀሐፊ አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ ችግሩ መፈተሽ አለበት ይላሉ።
ስራና ቢዝነስ በሚበዛበት ቦታም የሚሰጠው የነዳጅ ኮታና ስርጭት ችግር መፍጠሩን አስረድተዋል፡፡
የኢትዮዽያ የነዳጅ አቅራቢዎች ድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ እስመለአለም ምህረቱ የሚታየው ችግር ከ ኮንትረኦባንድ ጋር የተገናኘ አይደለም እጥረትም የለም ይላሉ፡፡
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Comments