top of page

ሰኔ 24፣2016 - በጥራት መጓደል ስሙ በተደዳጋሚ የሚነሳውን የአሌክትሪክ ገመድ ወይም ኬብል ችግር ለመፍታ በርትቼ እሰራለሁ ያለ ደርጅት ስራ መጀመሩን ተናገረ

  • sheger1021fm
  • Jul 1, 2024
  • 1 min read

በጥራት መጓደል ስሙ በተደዳጋሚ የሚነሳውን የአሌክትሪክ ገመድ ወይም ኬብል ችግር ለመፍታ በርትቼ እሰራለሁ ያለ ደርጅት ስራ መጀመሩን ተናገረ፡፡


ደርጅቱ ኤፍ ኤንድ ቲ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች አምራች የሚባል ሲሆን ባለቤቱም ቻይናዊ ዜጋ የሆኑት ሚስተር ፎ ናቸው፡፡


ኤፍ ኤንድ ቲ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች አምራች በአሁኑ ወቅት ደረጃቸውን የጠበቁ፣ ተፈላጊውን ጥራት ያሟሉ የተለያዩ የኤሌክትሪክ ኬብል ምርቶችን እና የኬብል ምርት ውጤቶችን በማምረት ላይ ይገኛል ሲሉ ሚስተር ፎ   አስረድተዋል፡፡


የደርጅቱ ፋብሪካ የሚገኛው በሰባታ ከታማ ሲሆን የተቋቋመውም በ 5 ሚሊዮን ዶላር ነው ተብሏል፡፡


በኢትዮጵያ ውስጥ የኮንስትራክሽን፣ የትራንስፖርትና የመሠረተ ልማት ዝርጋታ ማስፋፊያ ፕሮጀክቶች የኤሌክትሪክ ፍጆታ እና የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ ኬብሎች ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መጥቷል፡፡


በኤሌክትሪክ ማስተላለፍያ ኬብሎች ጥራት መጓደል ምክንያት የምርቶች ተዓማኒነት ጉዳይና የአገልግሎት ዘመን አጭር መሆን ከተጠቃሚው  ጎልተው ከሚሰሙ ቅሬታዎች መካል በቀዳሚነት  የሚነሱ ናቸው፡፡


ኤፍ ኤንድ ቲ የኬብል አምራች ድርጅት ለኢትዮጵያ ገበያ ጥራቱን የጠበቀ ፣የረዥም ጊዜ የአገልግሎት ዘመን ያለው የኬብል ምርት ማቅረብ ዋነኛ ትኩረቴ ነው ብሏል፡፡


ድርጅቱ ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣቱ በፊት በቻይና አገርም በተመሳሳይ ዘርፍ ላይ ተሰማርቶ መቆየቱን  ተናግሯል፡፡

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page