top of page

ሰኔ 22፣ 2016 ‘’ከሀገር ውስጥ ገበያ ባለፈ ለ23 የአፍሪካ ሀገራት ክትባቶችና መድሀኒቶችን እያቀረብኩ ነው’’ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት

ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት በስፋት ክትብቶች እና መድሃኒቶች ሲያመርት ከውጪ የሚያስገባቸው ግብአቶች እያጠረው መሆኑን ተናገረ።

 

ኢንስቲትዩቱ በዓመት 300,000,000 ዶዝ ክትባቶችን እያመረተ ለሀገር ውስጥ እና ለጎረቤት ሀገራት እያቀረበ ነው ተብሏል።

 

ይህ የተባለው የኢንስቲትዩቱ 60ኛ ምስረታ ሲከበር ነው።

 

ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ታከለ አባይነህ(ዶ/ር )ተቋሙ አሁን ላይ 23 የተለያዩ የእንስሳት ክትባቶች እና 12 ፈዋሽነታቸው የተረጋገጡ ክትባቶች እያመረተ ነው ብለዋል።

 

ክትባቶቹና መድሀኒቶቹን ከሀገር ውስጥ ገበያ ባለፈ ለ23 የአፍሪካ ሀገራት እያቀረበ ነው፤ በዚህም ሀገር የውጪ ምንዛሪ እንድታገኝ አስችሏል ይላሉ ዋና ዳይሬክተሩ።

 

እንደ ሀገር እና አህጉር አቀፍ የደስታ በሽታን ለማጥፋት እየተሰራ በነበው ስራ ክትባቶችን በብዛት በማምረት ለሀገር ውስጥና ለሌሎችም ሀገራት እያቀረበ ነበር ተብሏል።

 

ኢንስቲትዩቱ ክትባቶችና መድሀኒቶችን በስፋት ለማምረት አንዳንድ ከውጪ የሚያስገባቸው ግብአቶች እጥረት እየገጠመው ይህንን ለመፍታትም እየተሰራ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ታከለ(ዶ/ር) ተናግረዋል።


የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ሃብታሙ ኃይለሚካኤል፤ መንግስት ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት ካፒታል ወደ 2.6 ቢልየን ብርድ እንዲያድግ ያደረገ ሲሆን ሀገሪቱ ከዘርፉ የተሻለ ተጠቃሚ እንድትሆን ከዚህ በላይ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

 

 ኢንስቲትዩት ምርቱን ወደ አንድ ቢሊዮን ዶዝ የሚያሳድግ ቤተ ሙከራ ሊገነባ ሲሆን አሁን ከሚያመታቸው  ፈዋሽነታቸው የተረጋገጠላቸው መድሀኒቶች እና ክትባቶች በተጨማሪ ሌሎች አይነት ክትባቶች ለማምረት ማቀዱን ሰምተናል።

 

አዲስ የሚገነባው ቤተሙከራ ግንባታውን ሲጠናቀቅ አሁን እየተመረተ ያለውን የምርት መጠን በሦስት እጥፍ እንደሚያሳድገው  ተገምቷል፡፡

 

ግንብታውን ወደ ተግባር ለማስገባት የአዋጭነት ጥናት እየተከናወነ እንደሚገኝ እና ዓለም አቀፍ ጨረታ ወጥቷል ተብሏል።

 

በረከት አካሉ

 

Comentarios


bottom of page