top of page

ሰኔ 21፣ 2016 - ‘’ድጋሚ ምርጫ በተካሄደባቸው ክልሎች የቀበሌ ወይንም የወረዳ አመራሮችና የብልፅግና ፓርቲ አባላት መራጮች ላይ ጫና ሊያሳድሩ በሚችሉ መልኩ ሲሳተፉ አስተውያለው‘’ ኢሰመኮ

‘’ድጋሚ ምርጫ በተካሄደባቸው ክልሎች የቀበሌ ወይም የወረዳ አመራሮችና የብልፅግና ፓርቲ አባላት መራጮች ላይ ጫና ሊያሳድሩ በሚችሉ መልኩ ሲሳተፉ አስተውያለው‘’ ኢሰመኮ


ድጋሚ ምርጫ በተካሄደባቸው በተለያዩ ክልሎች ህጉ ከሚፈቅድላቸው ሰዎች ውጪ የሆኑ የቀበሌ ወይም የወረዳ አመራሮችና የብልፅግና ፓርቲ አባላት በምርጫ ጣቢያዎች ውስጥ መራጮች ላይ ጫና ሊያሳድሩ በሚችሉ መልኩ መራጮችን የመመዝገብ፣ የማነጋገርና የመሳሰሉት ድርጊቶች ላይ ሲሳተፉ አስተውያለው ሲልየኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ተናገረ፡፡


ኢሰመኮ ይህን ያለው ሰኔ 16/2016 ዓ.ም በ4 ክልሎች የተካሄደውን የ6ኛ ዙር ቀሪና ድጋሚ ምርጫ የሰብአዊ መብቶችን ክትትል በመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱ ነው፡፡


በአብዛኛዎቹ ምርጫ ጣቢያዎቹ ውስጥ ወይም በ500 ሜትር አቅራቢያ የደንብ ልብስ የለበሱ የፀጥታ አካላት ታይተዋል ያለው ኢሰመኮ፤ በምርጫ ጣቢያ ሀላፊ በግልፅ ካልተፈቀደላቸው በስተቀር በምርጫ ጣቢያ 500 ሜትር አቅራቢያ መገኘት አልነበረባቸውም ብሏል፡፡

ክትትሉ በተከናወነባቸው የተወሰኑ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ በህግ ከተፈቀደላቸው ሰዎች ውጪ ማለትም ከመራጮች፣ ከምርጫ አስፈፃሚዎች፣ ከእጩ ወኪሎች፣ ከታዛቢያዎች እና ከቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ አባላት ውጪ የሆኑ ሰዎች መገኘት አልነበረባቸውም ሲል ኢሰመኮ አስረድቷል፡፡


በልዩ ልዩ ምክንያት በህግ ከተፈቀዱ ቦታዎች ውጪ የሚደራጁ ምርጫ ጣቢያዎች ቁጥር በቀደሙት ምርጫዎች አንፃር የቀነሱ ቢሆንም በጅግጅጋ፣ በመስቃን እና ማረቆ ምርጫ ክልሎች ላይ በግለሰቦች መኖሪያ ቤቶችና በአንድ የሃይማኖት ተቋም ት/ቤት ውስጥ 5 ምርጫ ጣቢያዎች መኖራቸውን ኢሰመኮ ማረጋገጡን በሪፖርቱ አካቷል፡፡


የኢሰመኮ የክትትል ባለሙያዎች በተመለከቷቸው ምርጫ ጣቢያ ደረጃ እንዲቋቋሙ የሚጠበቁት የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴዎችም አልተደራጁም ብሏል፡፡


በድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ላይም ለሚነሱ አቤቱታ የምርጫ አስፈፃማዎች ምላሽ እንደሚሰጡ ኢሰመኮ ማረጋገጡ አስረድቷል፡፡


የድጋሚ ምርጫ በሚከናወንበት የምስቃንና ማረቆ ምርጫ ክልል ሰኔ 12 ቀን 2016 ዓ.ም የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳና የድጋፍ ሰልፍ ማካሄዱን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የክትትል ሪፖርት ጠቁሟል፡፡


ያሬድ እንዳሻው


Commenti


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page