top of page

ሰኔ 21፣ 2016 - ዘርፉ በክልሉ ያላደገበት ምክንያት ምን እንደሆነ ጠይቀናል

አጠቃላይ ካፒታላቸው ከስድስት መቶ ሺህ እስከ አስር ሚሊየን ብር የሆኑ እና ከስድስት እስከ ሃምሳ የሚሆኑ ሰዎችን፤ በስራቸው ይዘው የሚያሰሩ አምራች ኢንዱስትሪዎች አነስተኛ በሚል ይጠራሉ።


ካፒታላቸው ከአስር ሚሊየን እስከ ዘጠና ሚሊየን ብር የሆኑት እና ከሃምሳ አንድ እስከ መቶ ሰዎችን፤ ይዘው የሚያሰሩት ደግሞ መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች በሚል ይታወቃሉ።


እንደዚህ አይነት 25,200 አነስተኛ እና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች በአገር አቀፍ ደረጃ እንዳሉ ሠምተናል።


የእነዚህ ኢንዱስትሪዎች ስርጭት በክልሎች የተመጣጠነ እንዳልሆነ ግን የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት፤ የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ አቶ አሸናፊ መለሠ ተናግረዋል።


ለአብነትም በአፋር ክልል ስለሚገኙ አነስተኛ እና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች ብዛት ከአንድ መቶ አይበልጡም ብለዋል።


ዘርፉ በክልሉ ስላላደገበት ምክንያት ምን እንደሆነ ጠይቀናል፡፡



Comments


bottom of page